0
#FastMereja I አርቲስት አስቴር አወቀ እና ሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ዛሬ ህዳር 19/2017 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።
የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማቶችን እና የሚዲያ ሽፋኖችን በማግኘት እና የሀገሯን ሙዚቃ በድምቀት በማስተዋወቅ የምትታወቀው የሙዚቃ ንግስት አሁን ደግሞ ከሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት ጋር በህብረት በመሆን የተለያዩ የስነ ጥበብ፣ የበጎ አድራጎት እንዲሁም የሚዲያ ስራዎችን ለህዝብ እንደምታደርስ የአስቴር አወቀ ማናጀር ወ/ሮ አዳነች ወርቁ ገልጻለች።
የሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት የሽያጭ እና የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ተሬሳ እንደገለጹት በዚህም ስምምነት ለህዝብ መልካም ነገር የማድረስ እቅድ እንዳላቸው አሳውቀዋል።
ሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት በአሜሪካውያንና እና ቱርካውያን ባለ ሀብቶች የተቋቋመ ሪል እስቴት ሲሆን ከ 1000 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውን የስራ ዕድል ፈጥሯል። ላለፉት 3 አስርት አመታት በአሜሪካ እና በቱርከ እንዲሁም ለ9 ዓመታት በሀገራችን ኢትዮጵያ ስኬታማ የሆኑ እጅግ ዘመናዊ የሪል እስቴት ፕሮጀከቶችን በመስራት ላይ ይገኛል::




4 comments
😤😏👉
ጭራሽ እስካሁን በሂወት አለች😂
አስቱካ አረጀች😥
አሰቱካ 🥰