
#የካህኑን እጅ በደም ተነክሮ ሲያዩት ደንግጠው ወደቁአንድ ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማዊ በቅዱስ ስጋውና በክቡር ደሙ ላይ ዲያብሎስ ጥርጣሬ እየፈጠረ ይዋጋቸው ጀመር፡፡ ሁልጊዜም ሲቆርቡ ካሕኑ የሚሰጧቸው ህብስትና ዲያቆኑ የሚያቀብላቸው ወይን ብቻ ነው የሚታያቸውና መች ነው እውነተኛ ስጋና ደም የሚሆነው በሚለው ጥያቄ ተነስተው በጊዜ ብዛት ወደ ጥርጣሬ ሊገቡ ሆነ፡፡በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከእሳቸው በዓት አጠገብ ያሉ የበቁ አባት ዘንድ በመመጣት ችግሩን ይነግራቸዋል፡፡ እኒህ የበቁ አባትም ወደ ጎረቤታቸው ይመጡና ችግሩን የራሳቸው አስመስለው “አባቴ የምስጢረ ቁርባን ነገር ግራ አጋባኝ፣ አእምሮዬ እውነተኛ ስጋውና ደሙ ሆኖ የሚለወጠው መች ነው? እያለ በጥያቄ ሰላም ነሳኝ ይሏቸዋል፡፡ በነገሩ የተገረሙት አባትም እኔም እኮ የምነግረው አጥቼ እንጂ ተመሳሳይ ጥያቄ ወደ አእምሮዬ መመላለስ ከጀመረ ከራርሟል ይሏቸዋል፡፡ እርግጠኛ ለመሆን በቅዳሴ ጊዜ ካህኑ ስጋውንና ደሙን ሲፈትቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነው በማስቀደስ ለማየት ተስማሙ፡፡ በቅዳሴ ጊዜም ካህኑ ሕብስቱን አንስተው ሲፈትቱ ሰይጣን የሚፈትናቸው አባት የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ ሲያዩት ደንግጠው ወደቁ፡፡ አስገራሚው ነገር ከሁለቱ ባሕታውያን ውጪ ራሳቸው ቀዳሹ ካሕንም ሆኑ ሌሎቹ ልኡካን ይህን ምስጢር አላዩም፡፡ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ በሕብስትና በወይን መልክ ይሰጠን እንጂ የክርስቶስ አማናዊ ስጋና ደም ነው፡፡ ይህ ትልቅ ምስጢር የሚፈጸምባት ስርዓተ ቅዳሴው የሚካሄድባት ቅድስት ቤተክርስቲያንም የምስጢር መፈጸሚያ ስፍራ ነች፡፡ ለዚህም ነው ይህን ምስጢር የምንካፈልባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መርዳት፣ መስራት የሚገባው፡፡በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት ስር የሚገኘዉን ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ለመደገፍ እጃችንን እንዘርጋ፡፡ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444ለተጨማሪ መረጃ:- የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
0