የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል 10 ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኮርፖሬሽኑ በላከው አፊሴላዊ ደብዳቤ ገልጿል።
ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት ማደጋቸው የግል ዘርፉ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በአገልግሎት እና ሌሎች ልማታዊ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሳተፉ ለማበረታታት፣ የሀገሪቱን የውጪ ባለሀብት ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ እንቅስቃሴ ለማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ክላስተሮችን ለማስተዋወቅ፣ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ ንግድን፣ ዕቃን ወደ ውጭ የመላክ አፈፃፀም እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት አቅም ለማሳደግ፣ በዓለም ዓቀፍ የንግድ ሰንሰለት የሚኖር ቁርኝትን ለማስፋፋት፡ እና ዘላቂ ዕድገት ለማምጣት የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ ይታመናል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ደብረ ብረሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣
መቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና
ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡





3 comments
ቢያድጉ የኛ ህይወት 😭
ባያድጉ የኛ ህይወት 😭
እና
Burie