banner

በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ ስራ ተጀመረ

#FastMereja I ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን ከቴክኖ ሰርቭ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ህዳር 24/2017 ዓ.ም አስጀምረዋል ።

ጥምረቱ የስንዴ ዱቄት አምራች እና የምግብ ዘይት ፋብሪካዎችን በቫይታሚን በማበልፀግ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ተገልጿል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ አሁንም አሳሳቢ የሆኑ የአመጋገብ ችግሮች እያጋጠሟት መሆኑን የሚለርስ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢያቄም አምሳሉ ተናግረዋል።

ሀገራችን ከተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ጋር በተያያዘ 16.5 በመቶ አመታዊ ጂዲፒ ወጪ እንደምታደርግ የተገለፀ ሲሆን ይህንን ለማስቀረት በማሰብ በየዕለቱ ልንመገባቸው የምንችላቸው የምግብ ግብዓቶችን በቫይታሚኖች በማበልጸግ እንደሚሰራ ነው አቶ እያቄም የገለፁት።

ሚለርስ ፎር ኒውትሪሽን በአፍሪካ እና እስያ በሚገኙ ስምንት ሀገራት በባንግላዲሽ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ታንዛኒያ እና አሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደሚሰራ ተነግሯል።





1 comment

ሳሚ ነኝ December 3, 2024 - 12:23 pm

ያልተመጣጠነዉን በቀን አንዴ ባገኘው 😁

Reply

Leave a Comment