0
የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ በጥራት እና በፍጥነት ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የተገኙ ልምዶችን ቀምረን የጀመርነው 2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች አገልግሎት ክፍት ማድረግ በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት፣ ከኮንትራክተሮች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተወያይተናል።
በውይይታችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከመጀመሪያ ዙር አንጻር ሰፊ እና የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትብብር፣ በተያዘለት ጊዜ፣ በጥራት እና ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲያጠናቅቁ ተግባብተናል።
በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላታችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ እንደምንክሳችሁ ቃል ለመግባት እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
