0
ባቡል ኬይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ አስታዋሽ ያጡ ኢትዮጵያውያንን መሥራቾቹ የሰው ፊት እየገረፋቸው ህብረተሰቡን በማሥተባበር ሲረዱና ሲያስረዱ ቆይተዋል አሁንም በቀን ከ4 ሺ በላይ ወገኖቻችንን ይመግባሉ።
ይህን በጎና ደግ ስራቸውን የተረዳው በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ገንዘቡን እና ጊዜውን በመሥጠት የሚታወቀው ወጣቱ ባለጸጋ ምህረትአብ ሙሉጌታ በዛሬው ዕለት በባቡል ኸይር በመገኘት የ4 ሺ ሰው የምሳ ወጪ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ከመሸፈኑ ባሻገር ድርጅቱ እየሰራው ላለው በጎ ስራ ያግዝ ዘንድ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ምረትአብ ሙሉጌታ ዛሬ እዚህ ቦታ ተገኝቼ በእናት በአባቶቼ መመረቄና ያለኝን ማካፈል መቻሌ እድለኛ ነኝ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ቤት ሊጎበኝና ከጎናቸው ሊሆን ይገባል ሲልም መልዕክቱን አስተላልፏል።




