0
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታውቃል።
***
መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።
የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር ችሏል።
ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
የአዲስ አበባ ፖሊስ

10 comments
መቼ ነው የሚገሉን
ዘንባባወቹን አደራ ለኛ ችግር የለም
የከተማውን ነዋሪ በኑሮ ውድነት አስደንግጠችሁ መደንገጫ ሆርሞኑን ካጠፋችሁበት በኋላ ስለምን ድንጋጤ ነው የምታወሩት
በመሳሪያ ነዉ🙄😥
እኮ እየተኮሱ ገቡ ነው የሚለው ጉድ በል አድሳባ ነገ ደሞ ምን ይልኩብን ይሆን ? ሠላምታ በጥይት እሩምታ 🤭😢😢
ዘንባባዎቹን አደራ ለኛ ችግር የለውም😢😢
ትጥቅ ተይዞ ወደ ተሃድሶ ማእከል ኢላማ ነው እንዴ የሚሰለጥኑት😀
ኑሮ ያስደነገጠውን ሀበሻ ቶክስ መስማቱ ተስፋ ያስቆርጣል።
😭ምስክኑን የደሃ ልጅ የበላ ጅብ በሚለው ይስተካከል።
መሳሪያ ይዘው ነው እዴ ተሃድሱ የሚገቡት
ትጥቅ ሣይፈቱ ተሀድሶ አለደ ??