banner

በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው መዝሙረ ዳዊት መፅሐፍ ተመረቀ

#FastMereja I መዝሙረ ዳዊት መፅሐፍ ለአንባቢ እንዲገባ ተደርጎ የተፃፈው ዛሬ ሕዳር 29/2017 ዓም በአክሱም ሆቴል ተመረቀ።

መፅሐፉ በደብረብርሐን ሽሬ እንደስላሴ የኔታ ፅጌ ገ/ማርያም የድጓና የዝማሬ መስዋዕት መምህር የተዘጋጀ ሲሆን የቋንቋ አጠቃቀምና የአነባብ ስርአት በዜማ የተቀመጠ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ መፅሀፍ ለምእመኑ በሚመች መንገድ የቀረበ ሲሆን 633 የገፅ ብዛት እና 150 የዳዊት መዝሙሮችን የያዘ ነው ተብሏል።

በምርቃቱ ስነስርዓት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና በአዲስ አበባ በሚገኙ የድጓና የቅኔ መምህራን በተገኙበት ተመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን ቅኔና መወድስም ቀርቧል።

መፅሐፉ 700 የኢትዮጵያ ብር እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን በመንፈሳዊ የመፅሀፍት መደብሮች እንደሚገኝ ተገልጿል።





5 comments

Teddy Man Teddy Man December 8, 2024 - 6:45 pm

በልዩ ሁኔታ ማለት የእስካሁን ዝም ብሎ ነበር ምን ማለት ነው ለአንባቢው እንዲገባ ተደርጎ የተፃፈ ማለት ? ለገበያ ሲባል የሚደረግ ግር ግር ይቁም!

Reply
Mesay Gashahun December 8, 2024 - 6:45 pm

በአድስ መልክ ጥንቆላ ተሻሽሎ ቀርበ በመዝሙር ዳዊት ተብሎ ድግምት ልሰራ ስልጣኑ ይፍረስ

Reply
Melat Dada December 8, 2024 - 6:46 pm

የ መዝሙር 151አልበቃ ብሏችሁ መዝሙር 152 ጨመራችሁበት🙄🙄🙄

Reply
Iyesus Naw Tesfaye December 8, 2024 - 6:47 pm

Mn malet nw ahunim be Egzabiher kal lay macamar na makanas altawachum? Ye Egzabiher kal berasu yetazagaje nw enyan yazagajal enji enya esun mazagajat anchilim. Ere fatarin hunkan firut.

Reply
Getahun Dire December 8, 2024 - 6:49 pm

82ኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነዉ ?

Reply

Leave a Comment