0
ከታች ያለችው ልጅ ትላንት ሰይፉ ሾ ላይ ቀርባ ነበር። እናም ኩላሊቷን ታማ እያለች ድንገት ከተዋወቀችው ልጅ ጋር ፍቅር እንደ ጀመረች’ና ኩላሊቱን እንደሰጣት ተናግራ ህዝቡን ስታስገርመውና ስታስደንቀው ነበር። እኔም የተቆራረጠ ቪዲዮ አይቼ በልጁ ልብ እየተገረምኩ ነበር። ሰይፉ ፋንታሁን በታሪኩ ተገርሞ በተደጋጋሚ ‘ይሄ እኮ በፊልም መሰራት ያለበት ታሪክ ነው….’ ሲል ነበር። ልጅቷ ስለባሏ ስታወራ ‘ያኔ ዲያሌሲስ በማደርግበት ሰዓት በደንብ እንኳን ሳንተዋወቅ ለሰዓታት ከጎኔ አይለየኝም ነበር። ያኔ ከስቼ በገረጣሁ ሰዓት ነው ፍቅሩን ያሳየኝ…’ ምናምን ስትል ነበር !
አሁን እራሱ ባለታሪኩ በለቀቀው ቪዲዮ ግን እንደዛ ስታሞግሰው የነበረው ልጅ ከስቶ’ና እራሱን ጥሎ ‘ኩላሊቴን እሟ ቀሊጦ ካለቺኝ በኋላ ልጅቷ ትታኛለች። ከተለያየንም 3 ወር አልፎናል። እኔ በተራዬ ታምሜ አስታማሚ አጥቻለሁ። በዚህ ሰዓት እኔ ለቤት ኪራይ እንኳን የምከፍለው ነገር የለኝም….’ እያለ ነው።
Via ሙስተጃብ



10 comments
ፕራንክ ካልሆነ አደገኛ ጸብ ይነሳል ወንዶች💪
የኢትዮጵያን ፖለቲካ እሚያስንቅ ታሪክ🚶♀️🚶♀️🚶♀️
ኢቺ እከክ ህዝብ ልፋረዳት ይገባል😭
ሰይፉ ፋንታሁን ተው በዚህ ልክ ሕዝብ ላይ አታላግጥብን🤔🤔
የምር አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ! ሁለት ፍቅረኛሞች ናቸው አሉ ቤተሰብ አንድ ላይ እንዲሆኑ አልስማማ ሲሉ ራሳቸውን ለማጥፋት ወሰኑ! እናም ተራራ ላይ ወጡ! ከዛ እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም… ያንችን ሞት ቁሜ አላይም ያንተም ሞት ቁሜ አላይም ሲባባሉ ሰዓታት ፈጁ!
በመጨረሻም ወንድየው አይ እኔ ቀድሜ መዝለል አለብኝ ሲል ተስማሙ እሷ ልትከተለው! ከዛም እሱ ዘለለ! ለደቂቃዎች እሷ ስታስብ ቆየችና… ይቅርታ አድርግልኝ ፍቅሬ እኔ መሞት አልፈልግም አግብቼ ወልጄ መኖር እፈልጋለሁ ብላ ተመለሰች አሉ! እሱ ሞቶ ቀረ… ወዳጄ መጀመሪያ ነበር እንጂ አሁን እሷ ባንተ ኩላሊት ሌላ ጋ ትሆናለች
ኩላሊትህን ለእህትህ እና ለወንድምሽ ለልጅሽ ለልጅህ ብቻ ስጡ
በብሄር መባላቱን ትተን ይህንን ታሪክ እያነበባችሁ 🙏
እውነት ከሆነ ጊዜው አሁን ነው በሰቶች ላይ አድማ መምታት😕” አንድ ወንድ ለሁሉም ሁሉም ወንድ ለአንድ ወንድ” ዳይ👊💪
መጀመሪያም ሰይፉ ላይ አብሯት ባለመቅረቡ ጥያቄ ፈጥሮብኝ ነበር። እውነት ከሆነ ግን እጅግ አሳፋሪ ነው
ከብኩን ትውልድ ምን ይጠበቃል ጥሩ ነገር መስማት ይናፍቀናልኮ አንዳንድ ሴቶች ክፋታቸውን ሴጣኑ በራሱ አያውቀውምኮ።