ተጠርጣሪዎቹ ተሽከርካሪ በመከራየት በቂርቆስ፣ በቦሌ እና በጉለሌ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ሞባይል ስልክ እየቀሙ እንደሚሰወሩ ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል፡፡
ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው በተለምዶ ወሎ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ተጠርጣሪዎቹ በኮድ 2 A-28629 አዲስ አበባ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3 B-35824 አዲስ አበባ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር ለጥፈው ግምቱ 12ሺ ብር የሚያወጣ አይነቱ ሳምሰግ ሞባይል ቀምተው ይሰወራሉ፤ ወንጀሉን በፈፀሙ በአንድ ሰዓት ልዩነት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጉለሌ ሸገር አካባቢ ከአንድ ግለሰብ ላይ 8ሺ ብር የሚገመት ቴክኖ ሞባይል ይቀማሉ፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመያዝ በክትትል ላይ እያለ ወንጀሉን በፈጸሙበት እለት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። የቅሚያ ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በኮድ 2C -28629 አዲስ አበባ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3A-21634 አዲስ አበባ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር በመለጠፍ በተመሳሳይ የቅሚያ ወንጀል ለመፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሸዋ ዳቦ አካባቢ ተይዘዋል።
በተሽከርካሪ ውስጥ ከተለያዩ ግለሰቦች የተቀሙ ሶስት ሞባይሎች የተገኙ ሲሆን ከሶስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ሲሆን ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በቀን ገቢ ተሽከርካሪዎችን በመከራየት እና ሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር አዘጋጅተው በመለጠፍ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ወንጀል ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል። የሞባይል ቅሚያ የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ንብረታቸውን መረከብ እንደሚችሉም ተጠቁሟል።
ተሽከርካሪን ማከራየት የሚቻለው የህግ አግባብን ተከትሎ መሆን ስላለበት መኪና የሚያከራዩ ባለንብረቶች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ያስታወቀው ፖሊስ ህብረተሰቡ ተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት እንዳይፈፀም ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ባሻገር አጠራጣሪ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ቁጥር ካጋጠመው ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።



9 comments
ቂሊንጦም ኮዬም ነበሩ
ወዬ ወዬው የኔን ስልክ አራብሳ ዘርቀውኛል
እራሴ ጠርጥሬው ነበር 😎😎
ይሄ ኩላሊት የሰጠው አደል እንዴ
እንደዚህ አይነት እና መሰል ወንጀሎች ሲያጋጥሙ በየትኛው አድራሻ ነው የምንጠቁመው
ምንቀሳቀስ መኪና ነው ?ኤሄ
ምን ዋጋ አለው 2 ቀን ታስረው ይፈታሉ
C 37835 በሚል ታርጋ ቢትዝ መኪና ቅዳሜለት ከጠዋቱ 5ሰዓት አካባቢ ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካጋ ተመሳሳይ ድርጊት ፈፅመው ጠፍተዋል።።።
እኔኮ ግርም እሚለኝ ሲዘርፉ ከነሱ በላይ ሰው ያለ አይመስላቸውም ሲያዙ ደግሞ ሚስኪን ሚስኪን ያጫውታቸዋል በመጨረሻ ግን ምታ አይጠቅሙም