banner

FastPay የገንዘብ ማዘዋወሪያ መተግበሪያ ይፋ ሆነ።

#FastMereja I FastPay የገንዘብ ማዘዋወሪያ መተግበሪያ ዛሬ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተዋወቀ።

FastPay ከሀገር ዉጪ ለሚደረጉ ማንኛዉም የገንዘብ ዝውዉር ችግሮችን ለመፍታት ታስቦ እንዲሁም በሀገር ፍቅር ተነሳሽነት የሀገርን ችግር በሀገር ልጅ መፍታት በሚል መርህ የተመሠረተ መፍትሄ ሰጪ ቴክኖሎጂ እንደሆነ ተገልጿል።

የዲያስፖራውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ በአለም ዙሪያ ላሉ ሁሉ መፍትሔ ለመስጠት እንዲሁም የሀገርን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቀነስ ታስቦ የተሰራ ባለ ብዙ መፍትሄ አፕሊኬሽን ነው ተብሏል። በፋስት ፔይ የሚላክ ገንዘብ ምንም እንደማይቆረጥ ቀጥታ ወደ ፈለገው የባንክ አካውንት እንደሚገባ ተገልጿል።

FastPay በ2021 በWashington DC ሃሳቡ ተጀምሮ የገንዘብ ማስተላለፊያ ፈቃድ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ ማግኘት ከመቻሉም ባሻገር በኢትዮጵያ ዉስጥ ካሉት ከ30 በላይ ባንኮች ጋር ጥምረት መፍጠር እንደቻለሁ ገልጿል።

መተግበሪዉ Playstore እና Appstore ላይ ይገኛል።





Leave a Comment