banner

ቴክኖ በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በደማ

ቴክኖ በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በደማቅ ሁኔታ በስካይ ላይት ሆቴል አስተዋውቋል፡፡

በማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የቴክኖ ኢትዮጵያ ሃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡ ፕሮግራሙን የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸውም ቴክኖ ኢትዮጵያ በሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚናን እየተጫወተም እንደሚገኝ እና በዚህም ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው የገለፁ ሲሆን አክለውም ቴክኖ ኢትዮጵያም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በመቀጠልም በታዋቂው የቴኖሎጂ ኤክስፐርት አቶ ሰለሞን ካሳ ስለ አዲሶቹ የፋንተም V2 የታጣፊ ስልኮች ከቴክኖ ኤ አይ ጋር አጣምረው ስለመጡት ቴክኖሊጂ በምስል የታገዘ ሰፊ ማብራሪያ ለታዳሚው ተሰጥቷል፡፡
አዲሱ የቴክኖ ኤ አይ አጋዥ ቴክኖሊጂ የዕለት ተዕለት ኑሩን በእጅጉ ከማቅለሉም በላይ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመከወን የሚያስችል አጋዥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ተካቶለታል፡፡
በመድረክ የተዘጋጁ የተለያዩ ዝግጅቶች ጥሪ ለተደረገላቸው የዝግጅቱ ተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን ታዳሚዎች የቴክኖ ኤ አይ እና አዲሶቹ የፋንተም V2 ታጣፊ ስልኮችን በቅርበት የመመልከት ዕድልም እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪ ከኤ አይ ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ እንደ VR ያሉ የኤይ አይ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጌሞች ላይ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም የስልኮቹን የካሜራ ብቃት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ቀርቧል፡፡

ቴክኖ ከአለም የቴክኖሎጂ ገበያ ጋር ተወዳዳሪ የሆኑ እና ከፍ ያለ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ወደ ተጠቃሚ ማድረሱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ በኤይ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለተጠቃሚዎች አጅግ ቀላል እና ዘመናዊ የምርት ውጤትን ለመስጠት እየተጋ ይገኛል፡፡





Leave a Comment