banner

የ9 ልጆቹን እናት ያቃጠለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

#FastMereja I በስልጤ ዞን ምእራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪ የሆነው አቶ ተማም ሙዘይን የተባለ ግለሰብ ታህሰስ 17/2017 ምሽት 2 ሰአት አከባቢ ከሚስቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የፈላ ቡና የያዘ ጀበና ፊቷ ላይ የሰበረባት ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት እንዳደረሰባት ከፋስት መረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በቃጠሎ ከደረትዋ በላይ ሙሉ በሙሉ የተቃጠለች ሲሆን፣ ግራ ጆሮዋ ሙሉ በሙሉ መስማት አቁሞዋል ተብሏል።

አቶ ተማም ሚስቱን ካቃጠላት በኋላ ራሷን ስታ የወደቀች ሲሆን ከወደቀች በኋላ ማቃጠሉ ሳያንሰው በዱላ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅሞባት ከቤት ጎትቶ አውጥቶ ውጭ ጥሎዋታል ።

ግለሰቡ ይህን በጭካኔ የተሞላ ድርጊት የፈፀመው በጊዜያዊ ግጭት ነው ሲሆን ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

1 comment

Lidu Kl December 24, 2024 - 5:50 pm

አቤቱ ስንቱን ነገር ሰማን ስንቱን ነገር አየን …አሁንስ አይበቃንም ወይ?

Reply

Leave a Comment