banner

ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ በገደለው ተከሳሽ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ ተላለፈ

#FastMereja I የሃላባ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዛሬ ታህሳስ 16/04/2017 በዋለው ችሎት በሟች ሪባቴ ያሲን ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ባደረሰው በባሏ አቶ ሱልጣን ሙንድኖ ላይና በወንጀሉ ላይ በተዘዋዋሪ በመሳተፋቸው ጥፋተኛ ባላቸው ተከሳሾች ላይ እንደየወንጀላቸው የክብደት ደረጃ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከሳሽ የሀላባ ዞን ፍትሕ መምሪያ ዐቃብ ህግ የተከሳሾችን የወንጀል ዝርዝር ለሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም በሁሉም ተከሳሾች ላይ እንደየደረጃቸው ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚሁም መሠረት1ኛ ተከሳሽ አቶ ሱልጣን ሼህ ሙህዲን በአዲስ የትዳር አጋር ላይ አሰቃቂ ግድያ በመፈጸሙ ለሌሎችም አስተማሪ በሚሆን ደረጃ በሞት ቅጣት እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።

ከ2ኛ -7ኛ ያሉትን ተከሳሾችን ደግሞ (3ኛ ተከሳሽ ሲቀር) ሌሎቹን ተከሳሾች በ6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጡ ውስኗል።

በ3ኛ ደረጃ ስሙ የተጠቀሰውን ተከሳሽ ደግሞ ክሱ ጥፋተኛ ስለማያደርገው ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቷል።

8ኛ ተከሳሽ የጨቅላ ህፃን እናት መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት የ2 ዓመት የፈተና ጊዜ ተሰጥቷት ከማንኛውም የወንጀል ተግባር ታቅባ እንዲትቆይ የተወሰናባት የ6 ወራት ቀላል የእስር ውሳኔው ለሁለት ዓመት ታግዶ እንዲቆይ ብይን ሰጥቷል ሲል የሀላባ ቲቪ ዘገባ ያመለክታል።

7 comments

እዮብ መኮንን December 25, 2024 - 5:48 pm

የትኛው ነው

Reply
Mas Abawaji December 25, 2024 - 5:48 pm

የሚገርም ነው

Reply
Meki Abdi December 25, 2024 - 5:55 pm

ለስሙ ፂማቸውን አሳድገዋል😠
ሌላው ደግሞ የውሻ ሰንሰለት የሚያህል መስቀል አንገቱ ላይ አስሮ የሰው አንገት በቢላ ይቀነጥሳል😠
የመጨረሻው ዘመን (ቂያማ) መከራው ብዙ ነው😥

Reply
Hasan Ayele Motuma December 25, 2024 - 5:56 pm

የሞት ፈርድ እኮ የለም በሃገራችን

Reply
Henok Getachew December 25, 2024 - 5:56 pm

የት ነዉ afiganistan ነዉ???

Reply
Wubetu century metal works December 25, 2024 - 5:57 pm

ገና ዛሬ ጥሩ ዜና ዘገባችሁ ለሟች ነብስ ይማር 😭

Reply
Mulatu Muse Gebere December 25, 2024 - 5:57 pm

ዘገባው አወዛጋቢ ነው ማለትም ፊንጭ ለመርዳት ያስቼግራል

Reply

Leave a Comment