በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሙህር አክሊል ወረዳ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ዘልቆ በመግባት የምእመናን ጫማዎች የሰረቀው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተገለጸ።
ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ በጉራጌ ዞን በሞህር አክሊል ወረዳ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምቱ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ግድም በሀዋርያት ከተማ ወንጀል ለመፈፀም እንድያመቸው የተወሰኑ የማብራት ቆጣሪዎችን ካጠፋ በኋላ ሀዋርያት ፅርሀ ፅዮን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዘልቆ በመግባት ለህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለክብረ በዓል መጥተው ቤተ-መቅደስ ገረንገር ላይ ጫማቸው አውልቀው ቤተመቅደስ የገቡ የ9(ዘጠኝ ) ሰዎች ጫማ በለበሰው ጃኬት ሸክፎ ሲወጣ በክትትል በመፈፀሙ ከባድ የስርቆት ወንጀል በተመሰረተበት ክስ ነዉ።
ተከሳሹ የወንጀል ሪከርድ ያለበት መሆኑንና ፍርድ ቤት ቀርቦም የእምነት ክህደት ቃሉ እንዲሰጥ ተጠይቆ ክሱን እንደማይቃወም ወንጀሉን መፈፀሙ አምኖ በዝርዝር ያስረዳ በመሆኑና በሰጠዉ የእምነት ቃል መሰረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።
የሞህር አክሊል ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝን በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከምሁር አክሊል ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል።
Via: መናኸሪያ ሬዲዮ
6 comments
ሰው የደፈረ ና የገደለ በምህረት የሚኖርበት ሀገር ገና ጉድ ይሰማል😊
የትኛ እምነት ተከታይ ነው
ሰው ነፍስ ሰርቆ 10 ዓመት በሚፈረድበት ቀደም ሲል በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሪከርድ ከለሌው ወንጀሉ ከ18 ወር በላይ እንዴት ያሳስረዋል ?
ሲኦል ገባ አትሉም😂
9 ጫማ …9*2 =18 ድረድግ🙄😁
Mn Chegerot Yehun???