banner

በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ጉቦ የተቀበሉ የቁጥጥር ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ ተያዙ

በደረሰኝ ቁጥጥር 10ሺ ብር ጉቦ የተቀበሉ ሶስት የቁጥጥር ባለኑያዎች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የንፋስ ስልክ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሶስት የደረሰኝ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የ10 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

የገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ በተለይ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የአዲስ አበባ ቁጥር 2 የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ግብር ከፋይ የሆነ ግለሰብ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሆኑን ተናግረዋል።ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን የፈፀሙት አርብ ታህሳስ 11 ቀን 2017ዓ. ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፔፕሲ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጎልደን የታሸጉ ውሃዎች አምራችና አከፋፋይ ድርጅት ላይ ነው፡፡

ጥቆማው የደረሰው የክፍለ ከተማው ፖሊስ የምርመራ ስራ በማከናወን ከውሃ አምራችና አከፋፋይ ድርጅቱ ባለቤት ከሆኑ ግለሰብ ጥቆማው እንደደረሰው ተናግረዋል።የቁጥጥር ባለሙያዎቹ ከአንድ ሳምንት በፊት ከዚሁ ድርጅት የሽያጭ ባለሙያ ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር የ20ሺህ ብር ጉቦ መቀበላቸው በመረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል፡፡በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Leave a Comment