በሀይማኖታዊ ነገር የሚከራከሩም ሆነ የሚያስተምህሩ ሰዎች ሂክማ (ጥበብ ) ቢኖራቸው ብዬ እመኛለሁ ። የተረጋጉ ፤ አድማጭ ፤ እውቀት ያላቸው ፤ የሰውን ሀይማኖት የማይነኩ ፤ የማይጮኹ ፤ የሌላውን ሀሳብ የሚያከብሩ ፤ ብዙ ተጠይቀው በጥቂቱ የሚመልሱ ፤ ማብራራት የሚችሉ ፤ አንደበተ እርቱ ፤ የሚናገሩትን የሚኖሩ ፤ ወ.ዘ..ተ ቢሆኑ ብዬ እመኛለሁ ። አክሊል እነዚህን ያሟላ ወጣት ይመስለኛል ። በቃ የሆነ ጥንቅቅ ያለ ነገር አለው ።
ሙሊምም ሆነ ክርስቲያን ፔንጤም ሆነ ካቶሊክ ሚዲያ ላይ ወጥቶ ሲያስተምር ከሌሎች ሰዎች በተሻለ እውቀት’ና ጥበብ ሊኖረው ይገባል ብዬ አስባለው ። በተለይ በተለይ ለራሳቸው ሰበብ እየሰጡ ከእምነት ተቋማት እራሳቸው’ን ያገለሉ ሰዎችን በጥበብ መመለስ የሚችሉ ሰዎች መሆን አለባቸው ብዬ አምናለሁ ። አክሊልም ለዚህ የታደለ ይመስለኛል ። ከየትኛውም ሀይማኖት ጋር ሲነታረክ አታየውም ነገሮችን ቀለል ባለ መልኩ ያስረዳል ፤ ይወያያል ፤ የሌሎችን ሀይማኖት አይነካም ..! የራሱን አስተምህሮ ብቻ ለሰዎች ያጋራል ። ሲተች ፤ ሲጨቃጨቅ ፤ ሲሰዳደብ ፤ ስለማታየው እንድታየው ይጋብዝሀል ። እንደ አክሊል ያሉ ሲያስተምሩም ሆነ ሲወያዩ የሌሎችን ሀይማኖት ሳይነኩ ሳያንቋሽሹ መልዕክታቸውን በተገቢው መንገድ ማድረስ ለሚገባው ሰው የሚያደርሱ የሀይማኖት መምህሮች እንዲበዙ ምኞቴ ነው ።
በሙባሪክ ያሲን
10 comments
እንዲህ አይነቱን ከፊት ብናስቀድም ኖሮ ሌሎቹ ትኩረት ባላገኙ
ሙባረክ ያሲን🙏
እኛ ግን ምን መሰለህ ነገ እሱ ቢሰናከል ሌላ አኬ ደሞ በዘመናት መካከል ይነሳል ስለዚህ በሰው ላይ ጥገኛ ከመሆን መጠበቅ ይገባል እንላለን !
እንዲ ሚዲያ እና ሰው አይን ላይ ሚገቡ ሰዎች የሆነ ቡዳ ይበላቸዋል መሰል ይጰነጥጣሉ ጸልዩለት😋 ዘመኑ በቤቱ ይለቅ
እውነት ነው እጅግ መልካም ሰው ጥሩ አስተዋይ ውስጠ ወይራ ነው!! ብቻ እንደ ዳንኤል ክስረት አንዳቀይረው ነው…. እኛንም አተረፍን ስንል እንዳንከስር ብቻ እ/ር ይጠብቀው!!@
እውቀት ትህትና እና ፍቅር ከሌለው ባዶ ነው፣አኬ ደግሞ ታድሎታል፣በተለይ ከመፅሃፍቅዱስ እውቀቱ በተጨማሪ በተለያዩ ዘመናት ስለ ወንጌል የሰበኩትን የሊቃውንት መፅሃፍት ሚስጥራቼውን እና ትርጓሜአቸውን የተረዳበት መንገድ ፅድት ያለ ነው። ደግሞ ዘመናዊ አነጋገሩም ለሰው እንዲያዩት ያስገድዳል ። ቢያንስ ሰው ሁሉም እምነቱን እንዲጠይቅና እንዲያቅ ያደርጋል።አኬ በርታልን።
ፀሐፊውን ያስደሰተ አክሊል አንድ የተናገረው ነገር ያለ ይመስለኛል። በተለይ ጸሐፊው ተከራክሮ የተሸነፈበት ሐይማኖታዊ ጉዳይ ላይ አክሊል የተባለው የተናገረው ነገር። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ አይደል 😂😂
ገድል ተጽፎ ታቦት ተቀርጾ ቀን ተመድቦለት ቢመለክ ምን ይመስልሀል ???
ፈጣሪ የልብን እንጂ የአፍን/የአንደበትን/አይመለከትም!!!🙏
እናታቸው ታድለው❤️