0
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ በርካታ የነዳጅ ጭነት ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ከጅቡቲ ነዳጅ ከተጫነላቸው እስከ አስር ቀናት ያለፋቸው ቢሆንም መዳረሻቸው ላይ ደርሰው ግን ነዳጁ እንዳላራገፉ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ከደወሌ እስከ አዲስ አበባ ባሉ መዳረሻ ቦታዎች ተሽከርካሪዎቹ የቆሙበትን ምክንያት ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባላሳወቁበት ሁኔታ በየቦታው ቆመው ታይተዋል ሲልም ገልጿል፡፡
በዚህም የነዳጅ ማደያዎች በወር መገባዳጃ የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ይደረጋል በሚል ሰው ሠራሽ እጥረት እና በማደያዎች ረጃጅም ሰልፎችን እየፈጠሩ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በሚገባው ቀን በመዳረሻቸው ላይ ደርሰው የጫኑትን ነዳጅ ያላራገፉ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ በተመለከተ መረጃ እንዲቀርብለት ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ጥያቄ አቅርቤያለሁ ያለ ሲሆን ስለዘገዩበት ምክንያት በቂ ማስረጃ የማይቀርብለት ከሆነ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡
Via: ሀገሬ ቴሌቪዥን
2 comments
ቤንዚል ማደያ ውስጥ ጠፍቶ በችርቻሮ ግን 250 ብር እየተሸጠ ነው እዚ ላይ ከሰሞኑ የሚደረገው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ደሞ ሲጨመር በሊትር 350 👍
አብረው አይደል እንዴ ሚሰሩት