ዛሬ ጥር 15 ቀን 2017 የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮችን ወክለው በሰጡት መግለጫ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመበተን፣ ስርዓት አልበኝነትን ለማንገስ እና ሰራዊቱን ለመበተን ከተልዕኳቸው ውጪ ከህገወጥ ቡድን ጋር በመሆን በግልፅ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል።
ይህ መግለጫ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የማይታወቅ ሲሆን በማንኛውም መስፈርት ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። ጊዜያዊ ካቢኔው የሰራዊት አዛዦችን ያልተለመደ ውሳኔ ለማየት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። ሁኔታውን ከተመለከትን በኋላ ለህዝባችን ሰፊ ማብራሪያ እንሰጣለን ብለዋል።
የሰራዊቱን ከፍተኛ አዛዦች በመወከል የወጣው የዚህ ህገ መንግስት ይዘት በግልፅ መፈንቅለ መንግስት በማወጅ የፕሪቶሪያን ስምምነት አደጋ ላይ ጥሏል። መላው ህዝባችንን አደጋ ላይ የጣለ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔም ነው ይህ ወዲያውኑ መቆም አለበት ብለዋል። ይህ ካልሆነ የህዝባችንና የጸጥታ ሃይላችን አንድነት አደጋ ላይ ይወድቃል።
ሁሉም የጸጥታ ሃይሎች ይህንን ህገወጥ ውሳኔ ውድቅ እንዲያደርጉ እና ከዚህ ውጪ የትኛውንም ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዳያደርጉ እናሳስባለን ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው አስታውቋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
መቐለ
7 comments
ወልቃይት አማራ ነው ሌላው አይመልከተንም
መፈንቅለ መንግስት ይሁን መግነዣ መንግስት ሁሉም ትግራዋይ ከሰራዊት ጎን ነን
ያልሰለጠነ ክልል
አይደለም የጀመርነውን ጦርነት እጨርስ ነው ። ያው ካረባባ ኑሮ ይሻላል ሽራሮ ነው ነገሩ ። መልካም ጦርነት እች ምድር ያለ ጦርነት አትኖር
የበሠበሠ ዝናብ አይፈራም አለ ደ ፂ
እዚ ናይ ትግራይ ክልል ግዝያዊ ኣስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ዝተረኽቡ መግለጺታት ኣብ ክልሉ ዘሎ ግንኙነትን ሰላምን ንምዕራብ ትኩረት እንደምዝወስድ ይሰርሕ እዩ። እዚ ኣስኪርነት ዝበለ ኩነታት ህዝቢ ዕምነትን ሰላምን ንምግባር ብጥልቅ ምርካብን ትክክለኛ መፍትሒ ንምፍላጥ ኣስፈላጊ እዩ ዝብል። ኣብ ዝተኣኻኸለ መጠን ንምዕቃብን ንምስራሕን ነጻነት ዝመሰረተ መፍትሒ ንምርካብ ዕምነት እዩ።
ራያ ስለሆንህ አይወዱህም ወደ እናት ቤትህ ና