#FastMereja I ማርህይወት የእናቶች እና ህጻናት ልዩ የህክምና ማዕከል ዛሬ ጥር 17/2017 ዓም የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በተገኙበት ተመረቀ!
አቶ ሐብታሙ አሰፋ የህክምና ተቋሙ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ባደረጉት ንግግር ማርህይወት የእናቶች እና ህጻናት ልዩ የህክምና ማዕከል ራሳችን ባስገነባው ባለ 5 ወለል ህንጻ ላይ እንዲሁም ከ10 በላይ ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪሞችን በመያዝ ዘመናዊ ህክምናን በላቀ ደረጃ ለመስጠት ራዕይ ይዘን በ2017 ዓ.ም ጥቅምት ወር አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ብለዋል።
ለህክምና ቁሳቁስ ለግንባታና ለሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ከ340 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ወጪ እንደሆነ ተነግሯል።
ማዕከሉ በውስጡ እጅግ ዘመናዊ የቀዶ ህክምና ክፍሎች፣ እናቶች እና ህጻናት ተኝተው የሚታከሙበት መደበኛ እና VIP ክፍሎች፣ አርተፊሻል መተንፈሻ ማሽን ፣ የጨቅላ ህጻናት ጽኑ ህሙማን ክፍልን ጨምሮ እጅግ ዘመናዊ አልትራሳውንድ ፣ X-Ray እና የ ተሟላ የላቦራቶሪ ክፍሎችን የያዘ ማዕከል ነው፡፡ ስራ ከጀመረ ከጥቅምት 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ750 በላይ ታካሚዎችን አስተናግዷል፡፡
ከነዚህ አገልግሎቶች በተጨማሪ በቀጣይ አንድ አመት ውስጥ የተራቀቀ የመካንነት ህክምና እና ላፓራስኮፒ ወይም በካሜራ የታገዙ ቀዶ ህክምናዎችን ለመጀመር ታቅዷል፡፡
የህክምና ማዕከል ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ጸሐይ ኢነርጂን በመጠቀም ከአየር ብክለት የጸዳ 24 ሰዓት የማይቋረጥ የኤሌክትሪክ ሀይል ያለው ሲሆን በተመሳሳይ ደግሞ ራሱ ባስቆፈረው የከርሰ ምድር ውሃ ጽህናው የተጠበቀ ውሃን ያገኛል።
በዚህ ማዕከል ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ከፍተኛ የህክምና ባለሞያዎችን ጨምሮ በቋሚና በጊዜያዊነት ከ90 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡




