°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በዓለ አስተርዕዮን የአደባባይ በዓል ያደረገችው ጨንቻ ትጠራችኋለች።
እናቶች በዓሉን በጋሞኛ ዘዬ #አስቱራ_ማራሞ ይላሉ። በዓሉንም በዝማሬ ያደምቃሉ።
ጨንቻ የበዓሉ አከባበር በጣም አስደናቂ ነው። ከዓመት ዓመት ዝግጅት ይደረጋል። #የማህበረ_አስተርዕዮ ወጣቶች በማስተባበር፤ ሰንበት ተማሪዎች ደሞ ዓመቱን ሙሉ ባጠኑት ድንቅ ዝማሬ፤ ካህናት ከታቦታቱ ፊት በግዕዝ ወረብ፤ ምዕመኑም ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመዝሙርና በእልልታ ታቦቱን አጅበው የሰማዩን አገልግሎት በምድር ያሳያሉ።
ታቦተ ሕጉ ማለዳ ወደ ፀበል ወርዶ በእመቤታችን ፀበል ሕዝበ – ክርስቲያኑ ይጠመቃል። እዛው ፀበል ቦታ ብዙ የበረከት አገልግሎት ይከናወናል። ታቦተ ሕጉ ከፀበል ቦታው እስከ መንበሩ እስኪደርስ ከላይ የተገለጸው አገልግሎት እየተከናወነ ከተማይቱ ትባረካለች። ሕዝበ ክርስቲያኑም በአገልግሎት ለነፍስ የሚሆን ዋጋ ያገኛል።
እኔ አስተርዕዮ የሚለውን የቃሉን ትርጉም ከማወቄ በፊትም የእግዚአብሔር መገለጥ እንደሆነ ነፍሴ እንዲሁ አውቃዋለች። ምክንያቱም የእግዚአብሔርን መገለጥ ያለ ሥጋ እውቀት በመንፈስ የምንረዳው ነውና ነፍሴ ከስጋ በእውቀት ቀደመች። ለነፍሴ በመንፈስ የተገለጥክ ኃያሉ አምላክ ሆይ ተመስገን እያልኩ አስተርዕዮ በዓልን በየዓመቱ በደስታ አከብራለሁ።
ይህንን ደስታዬን ለሁሉ ለማካፈል ለበረከት ተሳትፎ ሁላችሁንም በክርስቶስ ፍቅር እጋብዛችኋለሁ። በጽሑፍ ብቻ መግለጽ ስለማይቻል መጥታችሁ እዩ። ማርያምን በፍፁም ደስታ ትሞላላችሁ።
ኑ በዓለ አስተርዕዮን በጨንቻ እናክብር!
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
ጌሻ ጌላኦ ማራሚ ናይቶ አኔ ኡባስ ጋthiቴ!
ኑ አዬይኮ ያና ማላ አሳ ኡባ ፄጊቴ
የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች:-
ትውልዱ ከበረከቷ ይካፈል ዘንድ በፍቅር ጋብዙ።
ይህንንም መልዕክት ለሁሉም እያጋራችሁ ጥሯቸው🙏
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
📷✍️ እስራኤል ኮከብ