በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በተወለዱ በ37 አመታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
ዶ/ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን ጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
10 comments
1 ሚሊዮን ሰው ነው የሞተው ብቻውን አይደለም። ነፍስ ይማር።
እጅግ ያሳዝናል ነፍስ ይማር!
Rip 😭😭😭😭
መተካት ቢቻል እኔ ማልጠቅመውን ገድለው፥አንተን ለሕዝባችን ቢተዉሉን። ወንድሜ ሐዘኔ ከልብ ነው፥አልቻልኩም።
በመከላከያ ሰራዊት ነው የተገደለው ምነው ሸፋፈናችሁት በብልፅግና ዘመን የአማራ ሙህራንን እየለቀሙ መግደሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል ,
Wuyy Dr andualem lasaw Hulu azagn doctor endet yigedelala gin 😭
ብቻውን አልሞተም በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ ነው የሞተው… .ነብስ ይማር 🙏🕊️
እጅግ በጣም ያማል 😭😭😭! ከእግዚአብሔር በታች ነፍስ የሚያድን ዶ/ርን ነፍስ የምትበላ አገር!😭 ያሳዝናል !!
ይህ ሰው ብቻውን አልሞተም ብዙዎች አብረውት ሞተዋል ያሳዝናል ነብስ ይማር😭😭
Huge loss for Peoples 😭😭