banner

ለጠ/ሚው መልእክት የህወሀት ምላሽ

ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ በትግሪኛ ቋንቋ የተላለፈውን መልእክት የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር «ማስፈራሪያ» ነው አሉ። ወይዘሮ ፈትለወርቅ ጦርነት አንፈልግም፥ ያለንን ጥያቄ ግን እናቀርባለን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል ሕዝብ በተለይም ለትግራይ ልሂቅ በማለት በትግርኛ ላሰራጩት መልእክት ምላሽ የሰጡት የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር፥ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ መልዕክት በጥሩ ቃላት የቀረበ እንኳን ቢሆንም የትግራይን ሕዝብ ለማስፈራራት ያለመ ሲሉ ኮንነውታል። ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ በጽሑፍ መልእክታቸው ባለፉት 100 አመታት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ባጋጠሙ ቅሬታዎች፥ የትግራይ መሬት የጦርነት ምድር ሆኖ ቆይቷል ያሉ ሲሆን የህወሓት ጽሕፈት ቤት ሐላፊ የሆኑት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ግን በምላሻቸው፥ የትግራይ ሕዝብ ባለፉት መቶ ዓመታት ወራሪዎችን መክቷል፣ ጨቋኞችን ታግሏል እንጂ የሆነ አካል ላይ ጦርነት የከፈተበት አጋጣሚ የለም ሲሉ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ ፈትለወርቅ፥ ያሉንን ጥያቄዎች እናቀርባለን ይህ ደግሞ ጦርነት መሻት አይደለም ብለዋል።

ወይዘሮ ፈትለወርቅ «ልዝብ የሚመስል ግን ደግሞ በውስጡ ተጠንቀቁ የሚል ማስፈራርያ ያለው ስለሆነ ወደጦርነት ያስገባል የሚል ስጋት በሕዝብ ዘንድ ፈጥሯል። ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ሕዝብ እንዲሸበር እየተደረገ ነው። ይህ በትግራይ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው በደል አካል አድርገን ነው የምንወስደው። የትግራይ ሕዝብ ይህ አይገባውም፣ ማስፈራራት አይገባውም። በመላው ትግራይ ያለው ሁኔታ ለጦርነት የሚጋብዝ ነገር የለም። መብታችን ይከበር፣ ማንነታችን ይከበር፣ በፕሪቶሪያ ውል መሠረት ሁሉ ነገር ይፈፀም ማለት ግን ጥያቄያችን ነው። ይህ ግን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አይደለም» ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ 50 ዓመት የምስረታ በዓሉን ሊያከብር ቀናት የቀሩት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፥ በታሪክ የከፋ የተባለ ክፍፍል ላይ ይገኛል። የምስረታ በዓሉን ለማክበር ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የየራሳቸውን የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረጉ ሲሆን፥ የየራሳቸውን የተለያዩ መፈክሮችም ይዘው ቀርበዋል። በትናንትናው ዕለት በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በመጪው የካቲት 11 የሚከበረው የህወሓት ምስረታ 50ኛ ዓመት ለማክበር ዝግጅት ላይ መሆኑን ሲገልጽ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን የሚመሩት ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ የካቲት 11ን ለማክበር ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል ብለዋል። በዚሁ መድረክ ስለወቅታዊ ሁኔታ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፥ የትግራይ ፖለቲካዊ ሁኔታ በከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና በሆነ ቅፅበት ግጭት ሊነሳ ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ጌታቸው «በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነን ያለነው። በሆነች ደቂቃ በአንድ ሰው ስህተት ወደ ግጭት የምንገባበት ዕድል የሰፋ ነው። እየሄድን ያለነው ወደ ጥፋት ስለሆነ ቢያንስ ይህ በዓል ቆም የምንልበት እናድርገው ነው እያልን ያለነው» ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ባለፈው ሰኞ ለትግራይ ብለው አስተላልፈውት በነበረ መልእክት የትግራን ልሂቃን የውስጥ ችግራቸው እንዲፈቱ እና ቀጥሎም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እንዲነጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባው የዶይቼ ቬለ ነው

10 comments

Amanuel Adamu February 6, 2025 - 6:26 pm

ሁለታቹም ገደል ግቡ ግን የደሀ ልጅን ተውት 🙏

Reply
Mifta Arebo February 6, 2025 - 6:27 pm

የሰው ልጅ አዕምሮ ባሰበውና በተረጎመው ልክ ይተረጎማል

Reply
Shoba Molu February 6, 2025 - 6:28 pm

እንዴ #ሞንጀሪኖ አለች እንዴ

Reply
Kb Diplomatic Leader February 6, 2025 - 6:28 pm

ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ የትግራይ ህዝብን ኣትወክልም😀

አመሰግናለሁ ።

Reply
Meha Moha February 6, 2025 - 6:29 pm

እና አሁን ከጦርነት ወደ ጦርነት ልትሸጋገሩ ነው በዝች ተራ ንግግር አይ ደሀው ሕዝብ ቆይ ምን ይሻላችኋል ሁለታቹም በቃ ግራ አታጋቡን ሰው በገዛ ሀገሩ ተርቦም ብሆን በሰላም ማረፍ አይችልም🤔

Reply
Mintesinot Mesele February 6, 2025 - 6:29 pm

ደግሞ እንደገና

Reply
Tilahun Chama February 6, 2025 - 6:30 pm

ቅርብ ጊዜ ሰማዕታትን ትቀላቀያለሽ በላት Fast Merja

Reply
Zelalem Gizaw Bekele February 6, 2025 - 6:30 pm

Furmenkella😭

Reply
Mintesinot Mesele February 6, 2025 - 6:30 pm

በጣም ነው እንደ የጠገቡት ወ/ሮ

Reply
Misikir Art February 6, 2025 - 6:30 pm

ጦርነቱን ጀምሩት እንጂ 💪

Reply

Leave a Comment