ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ አመት 61.9 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከአለም አቀፍ አገልግሎት 64.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቱ ተገለፀ።
#FastMereja I ኢትዮ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ የካቲት 5/2017 ዓም በዋና ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በስካይ ላይት ሆቴል ይፋ ተደርጓል።
በዚህም ከሐምሌ 2016 እስከ ታህሳስ 2017 በጀት ዓመት ያለውን የሥራ አፈጻጸም 3.24 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች በማፍራት አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ብዛት 80.5 ሚሊዮን መድረሱ ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የተገለፁ ቁጥሮችን ስንመለከት የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች
📌 የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 77.7 ሚሊዮን፣
📌 የሞባይል ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 43.5 ሚሊዮን፣
📌 የመደበኛ ብሮድባንድ 784.1ሺ
📌 የመደበኛ ስልክ የድምፅ ደንበኞች 765.6 ሺ ደርሷል፡፡
በሞባይል ኔትዎርክ በተከናወኑ የፕሮጀክት ስራዎች ተጨማሪ የ4.6 ሚሊዮን የሞባይል ኔትዎርክ አቅም በመገንባት 86.1 ሚሊዮን የነበረውን የሞባይል ኔትወርክ አቅም ወደ 90.7 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉ ተገልጿል።
በስድስት ወሩ 67 ተጨማሪ ከተሞች በድምሩ 491 ከተሞች የ4ጂ እንዲሁም 10 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡
የዋጋ ጭማሪውን በተመለከት የደንበኞችን የመክፈል አቅም መሰረት ያደረገ እና ለውጡ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚያስከትለውን የወጪ ጭማሪ እንዲሁም የአገልግሎት ቀጣይነትን ታሳቢ ያደረገ ነው የተባለ ሲሆን ጭማሬው ከተከሰተው ከፍተኛ የምንዛሪ ለውጥ አንጻር ጫናውን በመሸከም ጭማሬውን በተወሰኑ አገልግሎቶች ላይ ብቻ በማድረግ፣ የደንበኞችን የመክፈል አቅም፣ የኢኮኖሚ ጫና፣ እንዲሁም አካታችነትን መርህ ባደረገ መልኩ በማከናወን ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን እና በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 43% የሚሆኑት ላይ የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም ተብሏል።
ቴሌብር በግማሽ አመቱ 5 ሚሊዮን ደንበኞች በመመዝገብ አጠቃላይ የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 51.5 ሚሊዮን በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን የዕቅዱን 99.8% ማሳካት ተችሏል፡፡
በግማሽ አመቱ 1.03 ትሪሊዮን ብር የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር በቴሌብር የተከናወነ ሲሆን አገልግሎት ከተጀመረ ጀምሮ አጠቃላይ በኢኮኖሚው ላይ 3.58 ትሪሊየን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ አመቱ በተሰራው ረቂቅ የሂሳብ ሪፖርት መሰረት አጠቃላይ ገቢ 61.9 ቢሊዮን ብር በማስገኘት የእቅዱን 90.7% እንዲሁም ከአለም አቀፍ አገልግሎት የተገኘ ገቢ 64.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማስገባት የእቅዱን 63.8% ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች ቁጥርን በማሳደግ በሰራው መጠነሰፊ ሥራ ከአፍሪካ 1ኛ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተነግሯል።
10 comments
እየዘረፋችሁን☹️
Betam tinish new
Beyekenu iyezerefun adel inde
ማጅራት መቺ ተቋም😏
በጣም አሪፍ ዝሮፊያ ነው
እና እንደዛ እየዘረፉን ባያገኙ ነበር
እንደ አበላሉ አንሱዋችሁዋል😂😂😂😂
አረ የተዘረፍነው ከዚህም ይበልጣል #😭😭😭
.9ኙን አበድሩኝ🙌
I need some milk🥛
ብቻ 😁