በለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ተወካይ ዋና ሳጂን እንድሪስ ሁሴን እንደገለጹት መነሻውን ከከላላ ወረዳ መድረሻውን ደሴ ከተማ ያደረገው የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የካቲት 9/2017ዓ.ም ከጧቱ 12፡00 ስዓት ተከሳሽ ሁሴን አሊ የ12ኣመቷን ታደጊ ሀውለት ታደሰ አሰን የተባለችውን ህፃን ከመነሀሪያ ውጪ አሳፍሮ ወደ ደሴ ለመውሰድ ሲሞክር ተሳፈሪው ህብረተሰብ በሁለቱ መካከል የታየውን ልዩነት በመጠራጠር አቀስታ ከተማ ሲደርስ በከተማው ለሚንቀሳቀሱት ሰላም አስከባሪዎች ና ፖሊሶች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል፡፡
ተከሳሽ ሁሴን አሊ የከለላ ወረዳ 01 አቤት ውሃ ነዋሪ ሲሆን በከላላ ከተማ እራሱን የሀይማኖት መሪ /ሸህ/እና ደረሳ በማስመሰል ሲኖር ቆይቶ ታዳጊ ሀውለት ታደሰ አሰንን ከከላላ ወረዳ 02 ቀበሌ ቀርቀሬ ከምትባል ቦታ ፍየልና ከብት ከምትጠብቅበት የካቲት 8/2017ዓ.ም ከቀኑ11 ፡00 ከተናገርሽ አርድሻለሁ፣ እገልሻለሁ በማለት አስፈራርቶ አክስቱ ቤት በማሳደር ሊሰወር ሲሞክር መያዙን ገልጸዋል፡፡
ታዳጊዋ ጉዳት ሳይደርስባት እንድትገኝና ወንጀለኛውም በቁጥጥር ስር እንድውል ያደረገውን የአውቶቡስ ተሳፋሪ የከለላ ወረዳ ህዝብ እያመሰገን ሁሉም ህብረተሰብ ወንጀልን በማጋለጥ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንድቀጥል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ታዳጊዋን ለቤተሰቦቿና ተከሳሹን ለከላላ ወረዳ ፖሊስ እንደሚያስረክቡ ዋና ሳጂ እንደሪስ ሁሴን ገልጸዋል፡፡
የለጋምቦ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን
10 comments
አይ ኢትዮጵያ😞🎤
የደና ቁራን መስበስቢያ ሆኗል ሀገራችን💔💔💔
ጥሩ ነው ነገር ግን አስተማሪ የቅጣት ህግ የለማ………000000አይይይይይይ ዐዐዐኀኀ
አሁን በሞላ ሴት ይህ ህፃን ምን ሊያደርጋት አሰቦ ነው
ምን ልያረጋት?😥
እኒህ አይነት ክፉ ምግባር ያላቸውን ሰዎች ማጋለጥ መልካም እና ሁላችንም ከተባበርን ችግሩን መቀነስ እንችላለን።
የልጅቷ ፎቶ መለጠፉ ግን ትክክል ነው?
Inkuwan Allah xebeqesh
በቃ እስከዚህ ድረስ ነው የሚያስበው ጭንቅላቱ የሞተ ፈጣሪ እንኳንም ደረሰላት
ሁሌም የሚሰቀጥጥ ድርጊት መስማት ሰለቼኝ።ምንድነው የጎደለን በቃ ወደ ስርዓተ ጋሪዮሽ ዘመን ተመለስን?ልብ ይስጠን
በልብሱ ላይ በዱላ ብዛት ለቆ ነው🤔