0
#FastMereja I #ችሎት I የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።
በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።
ከቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በተጨማሪ ተመሳሳይ ክስ ተመሰርቶባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራም በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
Via: ቲክቫህ ኢትዮጵያ

6 comments
የታሉ
እውነተኛ ዳኛ እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ 🙏🙏🙏
ድሮስ ከስልጣን ማባረሪያ ሰበብ ነው እንጂ
ሌባ እንዴት ሌባን ይከሳል
እውነት ለውሸት እጅ ሰጥታ አታውቂም።እንኳን ለዚህ ቀን አበቃህ ጀግናው ፀግሽ!!
Zerefeh tfa enji kesun tashenfaleh be zerefkew genzeb malet yihe new
ጀግና የልማት ሰው።