banner

የከተማው ወጣቶች ፖሊሱን አመስግነው ሸኙ

#FastMereja I #ዜና I የዌራ ዲጆ ወረዳ ወጣቶች ባለፉት አምስት አመታት በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በፖሊስነትና በፖሊስ አዛዥነት የመራውንና ሰሞኑን በስራ አስፈላጊነት ወደ ዞን ለሄደው ረዳት ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ ስጦታና ሽኝት ተደርጎለታል።

ይህ ፖሊስ ወረዳውን በፖሊስ አባልነትና በዋና አዛዥነት ባገለገለባቸው ጊዜያት ለአባቶች፣ ለእናቶች፣ ለሴት እህቶች ለወንድሞች በቃ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍፁም አስተዋይና ለሁሉም የሚተናነስ ስናገር በአዳብ ሆኖ ህግን በግድ ሳይሆን በፍቅር በማስተማር ህዝብ ልብ ውስጥ መግባት የቻለ ሰው ነው።

ባለፉት አምስት አመታት ፍፁም በሆነ ቅንነትና ታማኝነት፣ በመተናነስ፣ ውብ ስነ ምግባርን በመላበስ በወረዳው በፖሊስ አዛዥነትና በፖሊስ አባልነት ለመራው ለረዳት ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ የምስጋና፣ የመልካም የስራ ጊዜና ሽኝት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በዛሬው ዕለት ለሱ ይገባል ይመጥነዋል ባንልም ካለን ላይ ቀንሰን ትንሽዬ ስጦታ በማዘጋጀት ከወረዳው ቅን ወጣቶች ጋር በመሆን የክብር እንግዶች በተገኙበት ሸኝተነዋል።

ረዳት ኢንስፔክተር ሁሲ አንተ ቅን ሰው መልካም የስራ ጊዜ ይሁንልህ!!!




8 comments

ስንታታ ቪዲዮ February 18, 2025 - 6:28 am

ይልመድብን🙏🙏

Reply
Belay Bekele February 18, 2025 - 6:29 am

መልካም ሰዉ ነው ❤❤❤

Reply
Mêqüanïnt Gödô February 18, 2025 - 6:30 am

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህይወት እያለ ማመስገን እየዳበረ መጧል ደስ ይላል። #እናመሰግናለን

Reply
Yaya Ye Buna February 18, 2025 - 6:30 am

👏👏👏👏

Reply
ዝም በል እስኪ February 18, 2025 - 6:31 am

God job

Reply
Walia Tadesse February 18, 2025 - 6:32 am

ጥሩ

Reply
Menen M Mesfin February 18, 2025 - 6:32 am

ደስ ይላል እንደዚህ ያሉትን እግዚአብሔር ያብዛልን አመስግኖ መሸኜት ደግሞ ማህበረሰቡ የስልጣኔን ማማ የተቆናጠጡ ይመስላል ይመቻችሁ

Reply
Fiker Getinet February 18, 2025 - 6:33 am

ወጣቶች ን አመስግኑልኝ

Reply

Leave a Comment