0
#FastMereja I ኬመቅድም ጄነራል አስመጪ እና ላኪ የሚድያ ኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምባሳደር በማድረግ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነን ዛሬ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ተፈራርሟል።
አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ የተመረጠችው ባላት መልካም ስም እና በታዳጊዎች ላይ ጭምር በምታሳድረው መልካም ተፅእኖ መሆኑ ተጠቅሷል።
ለአምባሳደርነቱ ስንት እንደተከፈላት ድምፃዊቷ «የጠየኳቸውን በቂ ገንዘብ ከፍለውኛል» ብላለች።
ሚድያ በ1968 በቻይና ውስጥ የተመሰረተ ሲሆን ከ200 በላይ ለሚሆኑ ሀገሮች ምርቶቹን ይልካል፣ በኢትዮጲያ የሚድያን ምርቶች ከ2018 ጀምሮ ኬመቅድም ጄነራል አስመጪ እና ላኪ በብቸኝነት የሚያስመጣ ሲሆን የቤት ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠብያ ማሽን፣ የእቃ ማጠብያ፣ የአየር ማቀዝቀዣ እና ማሞቂያዎች የተለያዩ መፍጫዎችን እና የመሳሰሉትን የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ለደንበኞች ያቀርባል።





1 comment
እንዴት ነው ብራንድ አምባሳደር ሚኮነው? ምን የተማረ ነው?