0
#FastMereja I ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ በዓድዋ ጂም የኢፍጣር መርሐግብር ማክሰኞ መጋቢት 9/2017 ዓ.ም አካሄደ። በጂሙ ውስጥ ለሚሰሩት የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በተሰናዳው የኢፍጣር መርሐግብር ላይ የኢፌዲሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ዲኤታ መኪዩ መሐመድ ተገኝተዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ ስፖርት ከሚሰጠው ጠቀሜታ ውስጥ አንዱ ወንድማማችነትን እህትማማችነትን ማጠናከር ፣የሀይማኖት መቻቻል፣ መከባበር ሲሆን ይህም በዓድዋ ጂም ውስጥ በዛሬው ምሽት በኢንስትራክተር ነፃነት ካሣ ፊትአውራርነት በተግባር በማየታቸው ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።
እንደዚህ ዓይነት መርሐግብሮች በጂም ውስጥ ያልተለመዱ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ መሳተፋቸው እንዳስደሰታቸውም ተናግረዋል።
በተጨማሪም በኢፍጣር መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የእስልምና እና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዓድዋ ጂም ይህንን ፕሮግራም ማዘጋጀቱ የእርስ በርስ ቀረቤታቸውን እንደሚያጠናክርላቸው እና የሀይማኖት ልዩነት በመካከላቸው መኖሩ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ገልፅዋል።




1 comment
ዘመዴ ናማ አፍጥር ቴምርም አለኮ😂