0
#FastMereja I የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰረት የፊታችን ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት በጊዮን ሆቴል አዳዲስ ሙዚቃዎችን በማካተት ለየት ባለ አቀራረብ ከአደናቂዎቹ ጋር ለመገናኘት መሰናዶውን ማጠናቀቁን ዛሬ ድምፃዊ ልዑል እና የኮንሰርቱ አዘጋጆች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።
ከልዑል ሲሳይ በተጨማሪ በመድረኩ ላይ ስካት ናቲ፣ ሃና ግርማ እና ዊሃ በዝግጅቱ ላይ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
ይህ በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የተዘጋጀው ኮንሰርት እንደተጠናቀቀ ግንቦት 2 በሀዋሳ፣ ግንቦት 23 በድሬደዋ ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በሦስቱም የኮንሰርቶች ላይ በአጠቃላይ ከ22 ሺህ በላይ ተመልካች የሚጠበቅ ሲሆን ቀድሞ ለሚገዙ ውስን የሚሆኑ ትኬቶችን 400 ብር መደበኛ 600 በዕለቱ በር ላይ 800 ቪአይፒ 2500 ብር ሲሆን ትኬቱን መግዛት የሚቻለው በቴሌ ብር ብቻ ነው ተብሏል።
ኮንሰርቱን ፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሀብ እና ሸጋ ኤቨንት በጋራ በመሆን አዘጋጅቷል።
#ኪነ_ጥበብ





2 comments
የዊሀን ድምፅ ከምሰማ እሬዲዮ ሲቋረጥ እሽሽሽሽ እሚለውን ድምፅ ብሰማ ይሻለኛል
ከፍለዉኝ አልገባም እስኪ 100ብር ያላቹህ ስጡኝ አሁን😭