#FastMereja I ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የ2 ሚልዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የሰላም ፕሮጀከት ማስጀመሩን ይፋ አደረገ
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ከGerman Foundation for World Population (DSW) እና Population, Health, and Environment Ethiopia (PHEE) ጋር በመተባበር በጦርነትና በሰላም እጦት ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑትን የማህበረሰብ ከፍሎች ለመደገፍ ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የ2 ሚልዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ Practice Peace and Live in Tranquility የተሰኘ የሰላም ሥራ ፕሮጀከት መጀመሩን ዛሬ ሚያዝያ 02/2017 ዓም አሳወቀ።
ይህ ፕሮጀከት በአፋር፣ በኦሮሚያና በሶማሊያ ከልሎች በሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች ላይ የሚተገበር ሲሆን የማህበረሰቡን ግንኙነቶች በማጠናከር በድጋሚ የሚቀሰቀሱ ግጭቶችን ለመከላከል፣ ለመቀነስ እና ለመግታት ታቅዶ የተዘጋጀ ነው።
አቶ ሣህለማርያም አበበ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ዳይሬክተር እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ማህበረሰብ ደህንነት ጉልህ ሚና ለሚጫወቱ የሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ የአካባቢ መሪዎችን፣ እንዲሁም ከማህበረሰቡ የተወጣጡ ሀገር በቀል ድርጅቶችን አቅም በማጎልበት አዎንታዊ ከባቢን ፈጥሮ ከመለያየት ይልቅ አንድነትንና መተሳሰብን የሚያስቀድም ህብረተሰብ ለመገንባት የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2027 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው ይህ የሦስት ዓመት ፕሮጀክት በትኩረት ስምንት አጎራባች ወረዳዎች ላይ የሚሰራ ሲሆን በቀጥታ 45,679 የሚደርሱ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ የሀይማኖት መሪዎችን እና የማህበረሰብ ተወካዮችን ሲደርስ በተዘዋዋሪ ደግሞ ከ782,000 በላይ ግለሰቦችን በተለያዩ መንገዶች ይደግፋል።
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ይህንን ፕሮጀክት የሚተገብረው ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ጋርበመተባበር ሲሆን የሚኒስቴር መስሪያቤቶቹ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይህንኑ ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን ፕሮጀከት በስካይላይት ሆቴል በይፋ ከፍቷል።
የአውሮፓ ህብረትም ይህን ፕሮጀከት መደገፉ በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍንና ጤናማ ማህበራዊ ትስስር እንዲሁም ዘላቂ ልማት ተበረታቶ እንዲቀጥል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።





6 comments
ሰላም በ 2 ሚሊየን € ብቻ ?🙄
ወይ ስላም ተስፋዬ🤔
ሰላምን ልገዙበት ነው 😄
በ2 ቢሊዮን ዮሮ ጦርነት
በ2 ሚሊዮን ዮሮ ሰላም
ቢያንስ የእናንተን ሆድ ይሸፍናል 🙌
የሰላም ምርትናምርታማነትን ለማሰደግ
በሰላም እንድንጥለቀለቅ፣ ሞልቶ ተርፎ ኤክስፖርት እንድናረግ መሰለኝ 🤔