#FastMereja I ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በሚያዚያ ወር በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን ሻምፒዮንስ አካዳሚ ይህን የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ከተጋባዥ እንግዶች፤ ከወላጆችና ተማሪዎች ጋር በመሆን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡
ሻምፒየንስ አካዳሚ ይህንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ላለፉት ተከታታይ ዓመታት በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ሲያክብር የቆየ ሲሆን አካዳሚው በኦቲዝም ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ከማስጨበጫ በዘለለ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ህፃናትን ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር አካቶ በሙያው በሰለጠኑ መምህራን እና ስራውን በሚከታተሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልጆችን በማስተማርና አመርቂ ውጤት በማምጣት ላይ ይገኛል፡፡
ሻምፒዮንስ አካዳሚ በኦቲዝም ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ከማስጨበጥ በዘለለ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ሕፃናትን ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር አካቶ በሙያው በሰለጠኑ መምህራን እና ስራውን በሚከታተሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልጆችን በማስተማርና አመርቂ ውጤት በማምጣት እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ባለቤትና የአዕምሮ ህክምና ባለሞያዋ መአዛ መንክር ተናግረዋል፡፡
ባለሞያዋ አክለውም የዚህ መርኃ ግብር ዓላማ የኦትስቲክ ተጠቂዎች መማር እንደሚችሉ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደሆነ ተናግረዋል። በእለቱ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ህፃናት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን አቅማቸውን ያሳዩ ሲሆን በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ቤተሰቦችም ልምዳቸውን አካፍለዋል።




