banner

ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ የእናት ባንክ ለእናቴ የጽሁፍ ውድድርን አሸነፈ!

#FastMereja I ሁለተኛው “ለእናቴ” እና “የአመቱ ድንቅ እናት” የተሰኘው የጽሁፍ ውድድር የመዝጊያ መርሃግብር ዛሬ ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ተከናወኗል።

በእናት ባንክ አማካኝነት ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው “ለእናቴ” ውድድር ሰዎች ስለ እናቶቻቸው ያላቸውን ስሜት በዝርው (ከግጥም ውጪ) በሆነ መንገድ (በወግ በመጣጥፍ በልብ ወለድ ወዘተ) የሚገልፁበት ሲሆን “የአመቱ ድንቅ” እናት የተሰኘው ውድድር ደግሞ ሰዎች በህይወት ያሉ እናቶቻቸውን አሊያም በአካባቢያቸውና በማህበረሰባቸው ውስጥ የሚገኙና ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ እናቶችን ታሪክ በፅሁፍ በምስል አሊያም በድምፅ በማቅረብ የተወዳደሩበት ነበር።

ለእናቴ” የጽሁፍ ውድድር አሸናፊች
1ኛ መላኩ ብርሃኑ /150ሺህ ብር/
📌 “የመኢሶኑ ሚስት” ዘመንን ታግላ ያሸነፈች ጀግና በተሰኘ ጽሁፍ

2ኛ ዳግማዊት ግርማ /125ሺህ ብር/
📌 ቀራንዮዬ ላይ ለተገኘሽው ትንሳኤ በተሰኘ ጽሁፍ

3ኛ መዝገቡ ልመነህ /100ሺህ ብር/
📌 “እናቴ ከብረት ይሆን የተሰራችው?” በተሰኘ ጽሁፍ

4ኛ እዮብ ጥላሁን /75ሺህ ብር/
📌 ለፈጣሪ የቀረበ እናትነት በተሰኘ ጽሁፍ

5ኛ አለሙ ቢያብል /50ሺህ ብር/
📌 እናት ልጅ አትመርጥም! በተሰኘ ጽሁፍ

🏆 የአመቱ ድንቅ እናት
ወይዘሮ የኔነሽ ፍሪሳ መርዳሳ ከኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦር ዞን ቆሎ ኮርማ ቀበሌ 200ሺህ ብር አክሲዮን ሽልማት አግኝቷል።





Leave a Comment