banner

የምሽት የኮሪደር የጎዳና ላይ ሩጫ ተዘጋጀ

#FastMereja I ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ተተኪ አትሌቶች ምቹ የመወዳደርያ ቦታዎችን መፍጠር እና የሀገራችንንም (የከተማችንን) ቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ እንደ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የድርሻችንን ለማበርከት የቀን እና የምሽት ሩጫ አዘጋጅተናል ሲሉ አዘጋጆቹ አፍላንዳን ሩጫ ዛሬ በግዮን ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።

የሩጫ ቱሪዝም በሀገራችን የተለመደ ቢሆንም የምሸት የኮሪደር የጎዳና ላይ ሩጫ በምሽት ታስቦ እና ታቅዶ ግን ሲደረግ በሀገራችን የመጀመርያው እንደሆነ ተነግሯል።

ውድድሩ የሚደረገው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ሲሆን መነሻውን በሴቶች አደባባይ አድርጎ በመርቅረዝ ሆስፒታል በመመለስ በዛው በካዛንችስ በኢተር ሌግዥሪ ሆቴል አድርጎ በውጭ ጕዳይ እና በፍልውህ መሀል አድርጎ ወዳጅነት ፓርክ የሚያልቅ ሲሆን 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ይሆናል።

በሩጫው ላይ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ በሙሉ ተጋብዘዋል።





2 comments

Yeabsira Berhanu May 9, 2025 - 2:07 pm

ልማት እሩጫ 😃

Reply
Yzebari Ka Lu May 9, 2025 - 2:08 pm

አብይ ይሳተፋል?

Reply

Leave a Comment