banner

ተሜ አፖልስትሪ አራተኛ ቅርጫፉን በሰሚት ከፈተ

#FastMereja I በቀድሞ ስሙ ተሜ ታፒሴሪ በአሁኑ ስያሜው ተሜ አፖልስትሪ አራተኛ ቅርንጫፉን በሰሚት ፍየል ቤት ዛሬ ግንቦት 30/2017 ዓም ከፍቷል።

ተሜ ታፒሰሪ በሀገራችን ዘመናዊ በሆነ መልኩ የመኪናን የውስጥ በመስራት እና በማሳመር እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው። የመኪና የታፒሴሪ ስራ ከዚህ ቀደም በልምድ ታግዞ በሀገራችን ይሰራበት የነበረ ቢሆንም ከነበረበት ደረጃ ዘርፉን በማሳደግ በሙያተኞች በማስተዋወቅ እና በማሰራት ስራውን የጀመረው ከ10 አመት በፊት በቤተል አንድ ቅርንጫፍ ሲሆን አሁን ላይ በከተማዋ ያለውን ተፈላጊነት በመገንዘብ አራተኛ ቅርንጫፍ በሰሚት ፍየለ ቤት ለመክፈት በቅቷል።

ተሜ ታፒሰሪ መኪናዎችን በተለያዩ ቅርንጫፎቹ ከመስራት በሻገር ሙያው በሰለጠኑ እጆች ፣ ጥራት ባለው እና ተወዳዳሪ ሊሆን በሚችል ደረጃ እንዲሰራበት በማሰብ ከሶስት አመት በፊት ተሜ የታፒሰሪ ማሰልጠኛ ከፍቶ እያስተማረ ይገኛል።

መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ቢሰጠው ከውጪ የሚመጣውን የአፖልስትሪ መስሪያ ግብዓት በሀገር ውስጥ ማምረት እንደሚቻል የተሜ አፖልስትሪ መስራች እና ባለቤት አቶ ተመስገን ዘየደ ገልጿል።

ተሜ አፖልስትሪ አሁን አዲሱን ቅርጫፍ ሳይጨምር 110 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ችለዋል።





Leave a Comment