banner

የEdTech ሳምንት የኢንቨስትመንት ፎረምና ዓወደ ርዕይ ተከፈተ

#FastMereja I ሪች ፎር ቼንጅ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የEdTech 2025 ሳምንት ለ2 ቀን የሚቆይ የኢንቨስትመንት ፎረምና ዓወደ ርዕይ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተከፍቷል።

“Innovate, Scale, transform: Unlocking the Future of Education Through EdTech” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ኢድ ቴክ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ ሀገራችን ለምታከናውነው ሁለንተናዊ እድገት በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሁሉን አካታችና ጥራት ያለው ትምህርት ለማዳረሳና የምንሻውን ልማት ለመገንባት ዘርፉን ልንደግፍ ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገራችን የትምህርቱን ዘርፍ ለማሳደግና አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ትምህርትን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት በትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንዴያ ገብረህይወት ናቸው።

የሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር መቅዲም ጉልላት ትምህርትን እና በሀገር በቀል ቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ የተሰማሩትን በማስተሳሰር ለሀገራችን የትምህርት እድገት አስተዋፆ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትምህርትን የሚያግዙ 11 የኢድቴክ ፈጠራዎችን በአውድ ረዕይ ላይ በዚህ ዙር እንዳቀረቡ ገልጿል።

11 ኤድ ቴክ ሶሉሽን ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ
ሲሆን ከ9 እስከ 12 ክፍል ተማሪዎችን የሚያግዙ ስራዎች እንደሆኑ ወ/ሮ መቅድም ተናግሯል።

የመድረኩ አላማ የሀገር ውስጥ የኤድቴክ(EdTech) ስራ ፈጣሪዎችን እና ስታርታፖችን በዘርፉ ፈጠራ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚያፋጥን ስነ-ምህዳር መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል።





Leave a Comment