0
#FastMereja I የሀገራችን ባህላዊ አልኮል መጠጦች መካከል ጠላ አንዱ ነው። የፈረንጆች የሆኑት ቢራ እና ድራፍት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው ኪስ እየጎዳ በመምጣቱ በተለይ የቢራ ወዳጅ የሆነው የከተማ ሰው ፊቱን ወደ ሐላ እያዞረ ይመስላል።
በትናንሽ የክፍለ ሀገር ከተሞች በቀላሉ የሚገኘው ጠላ አሁን አሁን በአዲስ አበባ ከፍተኛ ተጠቃሚ በማግኘቱ ትላልቅ ጠላ ቤቶች በመሃል ቦሌ እየተከፈቱ ይገኛሉ።
ጃምቦ ሃውስ በቀላሉ በየሰፈሩ የሚገኝባት አዲስ አበባ አሁን ወደ ጠላ ሃውስ እየተቀየረ ይመስላል።
የኑሮ ውድነት እና የቢራ ዋጋ ውድነት ሳይጠጣ እንዲያዞረው ያለው ወጣቱ ክፍል ቢራን ከመተው ይልቅ በቅናሽ ዋጋ የሚያገኘውን የሀገር ኬሚስትሪ የሆነው ጠላ እያዘወተረ እንደሆነ ተመልክተናል።
የአልኮል መጠኑ የማይታወቀው ጠላ በአንዳንድ ስፍራዎች በወረፋ እየተጠጣ “አለቀ” የሚባልበት የጠላ መሸጫ ቦታዎች አሉ።
ይህ መረጃ ሲለቀቅ በርካታ ወጣቶች ጠላን እየተጎነጩ እንደሚያነቡ ይገመታል።
ባትጠጡ ይመከራል፣ ካልጠጣው ሞቼ እገኛለሁ ካላችሁ በልክ፣ በኃላፊነት ይሁን!
ኧረ ጠላ ጠላ እኔን ጥልል ያርገኝ
እንቅልፌ ሳይመጣ እምታጋድመኝ!

2 comments
እና ብር ከቂጥ አይነጭ ከየት ይመጣል
😋😋