banner

የምግብ ቤቶች አዋርድ ሊካሄድ ነው!

#FastMereja I በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ምርጥ ምግብ ቤቶች በ10 በተለያዩ ምድቦች እውቅና ለመስጠት እና ለመሸለም ያለመ የbeU 2024 ምግብ ቤቶች ሽልማት ተዘጋጀ።

የምርጫ ሂደቱ የ2024 በተደረገ የደንበኞች እና ተጠቃሚዎች የመረጃ ጥናት፣ የትዕዛዝ ብዛት እና ጥራት፣ የደንበኞች አስተያየቶች፣ ከ5 ኮኮብ የተሰጣቸው የደንበኞች rating እንዲሁም በbeU ውስጥ ባሉ ሰራተኞች በስራቸው በአፈፃፀምና ባመጡት ተፅዕኖ የተሞላ ነጥበ መሆኑ ተገልጿል።

📌 ሽልማት የሚሰጥባቸው ዘርፎች

1. በbeU app ዘንድ ከፍተኛ ኮኮብ ያገኘ ምግብ ቤት
2. በደንበኞች ዘንድ ተወዳጅ
3. የምርጦች ምርጥ
4. አስደማሚ የምግብ አይነቶችን የሚያዘጋጅ ቤት
5. በጣም ፈጣን Delivery
6. ጥራት ያለው አስተሻሸግ
7. ለጤና ተመራጭ
8. ምርጥ ሀገርኛ ጣዕም
9. ምርጥ አለማቀፋዊ ጣዕም
10. ያልታወቀባቸው ግን በጣም ገራሚ ምግብ ቤቶች

በአስሩም ዘርፍ ሁለት ሁለት ተሸላሚ ይኖራል።

የሽልማቱ ስነ ስርዓቱ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል።

ከ1,200 ምግቦች ቤቶች ጋር አብሮ የሚሰራው BeU Delivery ከ3 ሚሊዮን በላይ ትዕዛዞችን አጠናቋን፣ 3000 ብስክሌተኞች እና ሞተረኞች አሉት።

ቢዩ ዴሊቨሪ ከቅሩንፉድ ዲጂታልስ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የመጀመሪያው የbeU ምግብ ቤቶች ሽልማት ነው።

#ኹነት


Leave a Comment