banner

አርተፊሻል ዳሌ የሚያስቀሩ ዘመናዊ የስፖርት ማሽኖች በEDF መግባታቸው ተገለጸ።

#FastMereja I ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ አዳዲስ ያስገባቸውን የስፖርት መስሪያ ማሽኖች ዛሬ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ለጋዜጠኞች አስጎበኘ።

ሰባተኛ አመት የምስረታ በዓል በቅርቡ የሚያከብረው ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ (EDF) ለምስራቅ አፍሪካ አዲስ ናቸው የተባሉትን የስፖርት መስሪያ ማሽኖችን አሟልቶ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የEDF መስራች እና ባለቤት ቶማስ ኃይሉ (ቶሚ ፕላስ) ገልጾልናል።

በአለማችን ላይ አርተፊሻል የሴት ልጅ መቀመጫ እየበዛ መጥቷል ይህም የሆነው ሰዎች ስፖርት ከመስራት ይልቅ በአቋራጭ ለማግኘት ስለሚፈልጉ ነው ይህ ደግሞ በራስ መተማመንን ያሳጣል ያለው ቶማስ አዲስ ያስገባናቸው ማሽኖች በጥንቃቄ ተመርጠው ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶባቸው ለሴቶች ዳሌ የሚሆኑ ዘመናዊ መሳሪያዎች በEDF እንደሚገኙ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በEDF የሚሰጡ አገልግሎቶች የዳንስ ፊትነስ፣ በዘመናዊ ማሽኖች ሙሉ የጂም አገልግሎት፣ ኪክ ቦክስ፣ ስፓ አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን በቅርቡ ራኒንግ ክለብ በአዲስ አበባ በEDF ይጀመራል ተብሏል።

ከአካል ብቃት እንቅስቃሴው በተጨማሪ ጤናማ አመጋገብ ምን መምሰል እንዳለበት በባለሞያ የታገዘ የምክር አገልግሎት በEDF እየተሰጠ ይገኛል።

በቀጣይ በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች ቅርጫፍ የመክፈት እቅድ እንዳለ የተገለጸ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ በዱባይ እና በሰሜን አሜሪካ EDF እንደሚከፈተ ተነግሯል።

EDF በአሁኑ ወቅት ለ45 ዜጎች የስራ እድል የከፈተ ሲሆን እየተስፋፋ ሲሄድ የዜጎች የስራ እድል የመፍጠር እድሉም እየጨመረ እንደሚሄድ ተገልጿል።





1 comment

Deme Vols Yasin Senayt June 28, 2025 - 1:55 pm

ግንትር ቂጥ መሆኑ ነው?

Reply

Leave a Comment