0
#FastMereja I አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር በማስገባት እና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች በተሻለ ጥራት የማምረት ስራ መጀመሩ ዛሬ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም በማምረቻ ማዕከሉ በተዘጋጀ መግለጫ ተነግሯል።
ከውጭ የሚገቡ ሶፋዎች በዲዛይን እና በውበት ተመራጭ ቢሆኑም በጥንካሬያቸው ክፍተት አለባቸው ያሉት የድርጅቱ ባለቤት አቶ ሙሉአለም ጌታቸው (ኪያ) የሀገር ውስጥ ምርት በማሳደግ በምቾት፣ በዲዛይን ፣ በውበት እንዲሁም በጥንካሪያቸው የሚዘልቁ ምርቶችን ለመስራት ተቋሙ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ከተመሰረተ 10 ዓመት ያስቆጠረው ብለስድ ሶፋ ማኑፋክቸሪንግ ትሬዲንግ ኩባንያ ከአርቲስት ሰላም አሻግሬ ጋር የብራንድ አምባሳደር ስምምነት አድርጓል።
ብለስድ ሶፋ ማኑፋክቸሪንግ ትሬዲንግ ኩባንያ የኪያ ፈርኒቸር እህት ድርጅት ነው።




