#FastMereja I በጋምቤላ ክልል ባህልንና ሀይማኖትን በሚፃረር አለባበስ ምሽት ላይ ሆቴል በመግባት የአልኮል መጠጥ ሲጠጡ የተገኙት ሴቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ::
የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ኚካሃ አኳይ ለወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደገለፁት በዲማ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ ሀይማኖትንና ባህልን በሚፃረር አለባበስ ከምሽቱ 4:ዐዐ ላይ ዳንስ ቤት በመገኘታቸው ጽ/ቤቱ ከፖሊስ ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ተናግሯል ::
ጽህፈት ቤቱ ከዚህ በፊትም 18 ዓመት ያልሞላቸው 9 ወንድ ህፃናት በምሽት መጠጥ ሲጠጡ በመገኘታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የገንዘብ ቅጣት ተቀጥቶ በዋህስ እንዲለቀቁ መደረጉን አስታውሰው የዛሬው ለየት የሚያደርገው ሀይማኖትና ባህልን በሚፃረር አለባበስ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ዳንስ ቤት መገኘታቸው ከባድ ያደርገዋል ብለዋል ::
በቁጥጥር ስር የዋሉት 4 ሴት ተጠርጣሪዎች በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ተገቢውን ቅጣት ተቀጥቶ እንደሚለቀቁ ገልፀዋል ::




10 comments
ተባረኩ ደግ አደረጋችሁ
ሙቀቱ ነው ወደው አይደለም
ውዝብላህ
ፓንትስ አድርገው ይሆን 🙄
ምነው ልብሱን ሳናወው ቆራረጣችሁት 🤭😁😁
እና ብርድ ልብስ ተሸፍነው ይጠጡ😊
ልብሳቸው ሙዚየም ይግባ 😁
ፖሊሶቹ ግን ?????.
የጋምቤላ ፖሊሶች ምነው አዲስ አበባ በተመደቡልን
እንደት ነበር የባህል አለባበሳችን በዋቃ ንገሩኝ
በስመአብ ለዛውም መስቀልም አለው🙄