banner

ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት ያዘጋጀው ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ መርሃ ግብር በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከፈተ

#FastMereja I 5ኛው ዓመታዊ ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች የተሰኘ አውደ ርዕይ ዛሬ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተከፈተ።

የዝግጅቱ መሠረታዊ ዓላማ በኢትዮጲያ ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ ውጤታማነትን ለማሻሻል በጥናትና ምርምር ውጤት ላይ በመመርኮዝ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እና የአነሥተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሠረታዊ ማነቆዎችን እና የብድር አቅርቦት ፈተናዎችን በመለየት የገበያ አውዱን ለማስፋት የሚቻልበትን መንገድ ማመላከት እንደሆነ የብሩ ማይንድ ኮንስልታንት ፒኤልሲ የኔትዎርኪንግ ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት አቶ መክብብ ዘሪሁን ገልጿል።

ፖሊሲ አድቮኬት ነው ምናደርገው ያሉትን ተግዳሮቶች እንዲታይ ያንን ተግዳሮት ደሞ አልፎ አድርጎ በተለይ ኤምኤሲዎች ገንዘብ ሚያገኙበትን ፋይናንስ የሚደረጉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይሄንን ፕሮግራም እንግዲህ በትልቁ ዲዛይን አድርገን የተነሳነው ሲሉ አቶ መክብብ አክሏል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ፕሮግራም ኤምኤሲዎች አክሰስ ቱ ፋይናንስ እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት በሚለው ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን በውይይቱ ላይ ፋይናንሻል ተቋማት፣ የመንግስት አካላት በዚህ ፕሮግራም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

በኤግዚቢሽኑ 40 ተሳታፊዎች ያሉ ሲሆን ከ4000 ሰው በላይ ጎብኚዎች ይጠበቃሉ።





1 comment

Eyasu Mulugeta Kulela July 3, 2025 - 5:18 pm

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከትላንትና ወዲያ የሰጠው ውሳኔም ሆነ ትላንትና ዕለት የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከFIFA, CAF እመራበታለሁ ከሚለው የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብና የስነ ስርዓት ህጎች ጋር ግልፅ መጣረሶች ያሉት በመሆኑ እንቃወማለን፡፡

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች።❗

Reply

Leave a Comment