0
#FastMereja I ግሪን ዌቭ አሊያንስ ከጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አርቲስቶች፣ ሙዚቀኞች፣ አትሌቶች፣ ቲክቶከሮች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋምቤላ ገብተዋል።
ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከልዑካኑ መካከል የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢፋ ሙለታን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና ታዋቂ አርቲስቶች ይገኙበታል።
የልዑካን ቡድኑ በጋምቤላ በሚኖራቸው ቆይታ በነገው ዕለት በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።




