#FastMereja I ኢትዮ IQ የትምህርት አማካሪ ድርጅት እና Anu parenting solutions በጋራ ለመስራት በዛሬው እለት ስምምነት አድርጓል። ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የተስማሙባቸው ነጥቦች አንዱ ሁሉም ወላጅ ተጋባዥ የሚሆንበት በወር ሁለቴ የሚዘጋጅ ሴሚናር ሲሆን በዚህም ወላጆች ያሉባቸውን ችግሮች የሚፈቱበት መፍትሄ ይዘው ይሄዳሉ ተብሏል።
ሌላው ልጆች ዝግጁ እንዲሆኑ ለምሳሌ ፈተና ሲደርስ ሊሆን ይችላል ስትረስ ያጋጥማቸዋል በዚህ ሰዓት ላይ ፈተና ሲደርስም ወይም ከዛ በፊት ያጠናን ዘዴ እና እንዲሁም ስትረስ ማኔጅመንት ግሩፕ ቴራፒ፣ ግሩፕ ሴሽኖች ለልጆች እንሰጣለን ብሏል።
ለመጀመር ያህል ኢትዮ አይኪው የራሱ አፕሊኬሽን ስላለው ከአኑ ፓረንቲንግ ሶሉሽን ጋር አንድ ላይ በመሆን የሚዘጋጅ የተለያዩ ኢቡኮች እንዲሁም ደግሞ መማሪያ መሆን የሚችሉት ትሪቪያ ጥያቄዎች፣ ፍላሽ ካርዶች ይኖራሉ በዲጂታል መንገድ ይሄንን መክፈል የሚችለውም የማይችለውም ማህበረሰብ ገብቶ አክሰስ ማድረግ የምንችላቸውን ጎን ለጎን አብረን የምናያያዝ ይሆናል ብሏል።
ሌላኛው ከትምህርት ቤቶች ጋርም አንድ ላይ ለመስራት ሂደቶችን መጀመራቸውን ገልጿል።
አኑ ፓረንቲንግ ሶሉሽን 2015 ዓ.ም የተመሰረተው ሲሆን ትኩረቱን ቤተሰብ ላይ ያደረገ ድርጅት ነው። ኢቲዮ አይኪው ከተመሰረተ ከአራት አመት በላይ ሆኖታል። በዚህ አራት አመት ጊዜ ዉስጥ ለተማሪዎች የአካዳሚክ ወይም በትምህርታዊ ያለ ስኬታቸው ላይ እንዴት መስራት ይቻላል የሚለው ላይ ሲሰራ ቆይቷል።



