0
#FastMereja I የቀድሞ ኪድስ ፓራዳይዝ አካዳሚ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በአዲስ ስያሜ ሁለት አዳዲስ ቅርንጫፍ ት/ት ቤቶችን በመክፈት ምዝገባ ማካሔድ መጀመሩን አስታወቀ ።
ዛሬ በተካሔደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተቋሙ ባለቤት አቶ ታደሰ ጥበበ እንደተናገሩት አዳዲሶቹ ት/ት ቤቶች ቦሌ ደምበል ጀርባ ጋዜቦ አደባባይ አካባቢ የሚገኘው ” ኢንተሌክችዋል አካዳሚ ” እና እንዲሁም ሐያት አካባቢ የሚገው ” ቡርቃ ሾቤ ት/ት ቤት ” ናቸው ።
እነዚህ አዳዲስ የትምህርት ተቋሞች የተሟላ የመማር ማስተማር አገልግሎትን ለመስጠት እጅግ ምቹ በሆነ ሁኔታ የተደራጁ መሆኑ ተነግሯል፣ ተቋሙ በሁለቱም ቅርንጫፍ ት/ት ቤቶች ለመጪው የ2018 የት/ት ዘመን አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ከወዲሁ ምዝገባ የጀመረ መሆኑን በዛሬው እለት በተካሔደው የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል ።
ተወዳጁን ተዋናይ ይመር አባተንም የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር በማድረግ ስምምነት ፈፅመዋል ።





3 comments
ጠመንጃ ያዥ ትምህርት ቤት አጠገብ ነው የምን ደንበል ነው?
ፓራላይዝ ፓራዳይዝ ምናምን ከሚሉት በሀገራችን ቋንቋ❤
Yehe besbese kadree ambassador adergut