0
#FastMereja I ኩዊንስ ኮሌጅ ለ25ኛ ጊዜ ዛሬ በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን በድምቀት አስመርቋል።
ኩዊንስ ኮሌጅ በዛሬው እለት በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም 2,614 ተመራቂዎች፤ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ደግሞ 1,582 በአጠቃላይ 4,196 ተማሪዎችን በዛሬው እለት ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ዋናው ጊቢ በሚገኘዉ ልደት አዳራሽ በድምቀት ሲያስመርቅ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሞገስ ግርማ ለተመራቂዎች ልዩ መልዕክት አስተላፈዋል።
ተቋሙ በቅድመ ምረቃ መርሃግብር ያስመረቃቸው ተማሪዎች በአካዉንቲንግና ፋይናንስ እንዲሁም በማኔጅመንት ትምህርታቸውን የተከታተሉ እንደሆኑ ተገልጿል።
በቴክኒክ እና ሙያ መስክ የተመረቁት ደግሞ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፤ በማርኬቲንግ እና ሴልስ ማኔጅመንት፣ በሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ሲክሬተሪ እና ኦፊስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሃርድዌር እና ኔትዎርኪንግ ሰርቪስ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
ኮሌጁ ከተቋቋመ ጀምሮ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ በዲግሪ እና በማስተርስ ፕሮግራም ከ50,000 በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል፡፡




