#FastMereja I ኤን.ኤም.ሲ ሪል እስቴት በዛሬው እለት አለም ባንክ ቱሉ ዲምቱ በሚገኘው የኤን. ኤም. ሲ የግንባታ ቦታ ላይ የተጠናቀቁት 45 ቤቶች ምርቃት እና ቁልፍ ርክክብ አደረገ።
እንዲሁም በድርጅቱ ለሚደገፉ 200 ህጻናት እና 300 አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች አስቤዛ ድጋፍ ተደርጓል።
የኤን.ኤም.ሲ ሪል እስቴት መስራች እና ባለቤት አቶ መሰረት መኮንን ሙሉ ወጪያቸውን በመቻል እያስተማሯቸው የሚገኙ 200 ወላጅ አልባ ህፃናት ያሉት ሲሆን በተጨማሪም በበዓላት ጊዜ አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የአስቤዛ ድጋፍ በማድረግ ይታወቃሉ።
በሪል እስቴቱ ልማት ላይ ከድርጅቱ ጋር አብረው ለሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት፤ ግለሰቦች የጋራ አልሚዎች የእውቅና ሰርፍኬት እና ዋንጫ ተሰጥቷል።
ኤን.ኤም. ሰ. ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በንግድ ስሙ ኤን ኤም ሲ ሪል ስቴት በ2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወስኖ በሊዝ በተሰጠው 35000 ካሬ መሬት ላይ ከ1000 በላይአፓርታማ ቤቶችን ፣ሞሎችን እንዲሁም 63 ጂ+2 ቤቶችን ለመገንባት አስቦ 41 ጂ+2 ቤቶችን እውቀትና ሀብት ካላቸው ግለሰቦች ጋር በጋራ አልምቶ በመገንባት በአዲሱ ሪል እስቴት አዋጁ መሰረት የግንባታውን 80% በላይ ለአጠናቀቁና የሚጠበቀባቸውን ክፍያዎች በወቅቱ ለከፈሉ የጋራ አልሚዎች በነሀሴ 7 ቀን 2017 ዓ/ም በሸራን አዲስ ሆቴል እና በነሀሴ 10 ቀን 2017 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል ይይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና ቁልፍ አስረክቧል፡፡
ኤን. ኤም. ሲ ሪል እስቴት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የቤት ችግር ለማቃለል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በሚገመት ካፒታል የተጀመረው የድርጅቱ የግንባታ ስራ 576 አፓርትመንት ቤቶችን ሰርቶ የማጠናቀቅ እቅድ እንዳለው ተገልጿል።
በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ተሠማርቶ የሚገኘው ኤን.ኤም. ሲ ሪል ስቴት በአሁን ወቅት እህት ኩባንያ ከሆነው ቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጋር በመተባበር በሪል እስቴት በማኒፋክቸሪንግ፣ በሆቴል፣ በትራንስፖርት፣ በቱርናትቭል፣ በአስመጪና በላኪነት፤ በመኪና ኪራይ ተሰማርቶ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡




