banner

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ 2465 ተማሪዎችን አስመረቀ

#FastMereja – ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2465 ተማሪዎች ዛሬ ነሃሴ 24/2017 ዓ.ም አስመረቀ።

በቴክኒክና ሙያ ፕሮግራሞች (አካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ ማርኬቲንግ፣ ሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት፣ ሴክሬተሪና ኦፊስ አድሚኒስትሬሽን፣ ሃርድዌርና ኔትዎርኪንግ) 709 ተማሪዎች ሲሆኑ፣

በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች (አካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ ማኔጅመንት፣ ኮምፒውተር ሳይንስ) 1756 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቋል።

ኮሌጁ በቀጣይ ከአለማቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑን ተገልጸዋል።

ኮሌጁ በማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት የነጻ ትምህርት መስጠት፣ የክፍያ ቅናሽ እና ሌሎች የማህበረሰብ ድጋፍ ተግባራትን እየሰጠ ሲሆን በቀጣይ በሰፊው እንደሚቀጥል ተነግሯል።





Leave a Comment