banner

ስታር ዋይድ አዋርድ ተካሄደ።

#FastMereja – በከለር ፉል ኤቨንት ኦርጋናይዘር የሚሰናዳው ስታር ዋይድ አዋርድ በተለያዩ ዘርፉ ተሰማርተው ለሀገራቸውና ለማህበረሰባቸው በጎ ነገር የሰሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ለማመስገንና ለመሸለም የተሰናዳው መርሃ ግብር ዛሬ ነሃሴ 24/2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል።

የህይወት ዘመን ተሸላሚ አንጋፋው ጋዜጠኛ ኢሳይ ሆርዶፋ እና አስካለ ተስፋዬ ተሸላሚ ሲሆኑ፣ ምርጥ ኤክስፖርተር በመሆን አቶ አብዱልሃኪም መሐመድ እና ስሁራ እስማኤል ተሸላሚ ሆኗል።

በምርጥ አስመጪነት አቶ በላይነህ ክንዴ እና አቶ ያደታ ጁኔይዲ ተሸላሚ ሲሆኑ በስራ ፈጠራ አቶ ሰቢር አርጋው እና ጠንክር ተኒ ተሸልሟል። በሴት ስራ ፈጠራ ሳምራዊት ፍቅሩ እና ተሲ ሩሳጋራ ተሸላሚ ሆኗል።

የዓመቱ ምርጥ ሆቴል ሸራተን አዲስ ሆቴል እና ኢሊሊ ሆቴል ተሸላሚ ሲሆኑ አዋሽ ባንክ እና አቢሲኒያ ባንክ የአመቱ ምርጥ ባንክ ሽልማትን አሸንፏል።

የአመቱ ምርጥ ኮንስትራክሽን አቶ ገምሹ በየነ እና ኢ/ር ዘለላም ወልደአማኑኤል ተሸልሟል። በሪል እስቴት አቶ ገብረየሱስ ኢገታ እና አቶ ዮናስ ታደሰ ተሸልሟል።

በአመቱ ምርጥ የግል ዩኒቨርሲቲ አቶ ድንቁ ደያስ እና አቶ ፈይሳ አራርሳ ሲሸለሙ ሀገር በታማኝነት በማገልገል ዘርፍ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተሸልሟል።

በማህበራዊ ሚዲያ ጉርሻ ፔጅ እና ሞኔት ቤክሲሳ ሲሸለሙ በዓመቱ ምርጥ Philanthropist ሽልማት ፍራኦል ኢትቻ እና ሜላት ንጉሴ ተሸልሟል።

#ማህበራዊ #ኹነት





Leave a Comment