#FastMereja – የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እና የመከላከያ ሚንስትር የነበሩት አቶ ለማ መገርሣ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አትዮጵያውን ስንከፋፈል ሳይሆን ስንተባበርና አንድ ስንሆን የማንሠራው ድንቅና ደማቅ ታሪክ እንደሌለ አመላካች ነው” ሲሉ የፕሮጀክቱን ምርቃት ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ገለፁ።
“እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከደሃ እሰከ ሀብታም ይህንን ግድብ ለመገንባት የአቅሙን ያህል ሀብት በማዋጣት አሻራውን ያሳረፈበት ታሪካዊ ግድብ ነው” ያሉት አቶ ለማ አክለውም በመላው የኢትዮጵያውያን ተሳትፎና ጥረት የተገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠዋል።
“ይህም የሚያሳየው ስንከፋፈል ሳይሆን ስንተባበርና አንድ ስንሆን አትዮጵያውን የማንሠራው ድንቅና ደማቅ ታሪክ እንደሌለ ይህ የህዳሴ ግድብ የክፍለ ዘመኑ ህያው ምስክር ነው” ሲሉ በመግለጽ፣ “መላው ኢትዮጵያውያን ምንግዜም አንድነታችን የድላችን መሠረት መሆኑን በመገንዘብ ለነገይቱ የተሻለች ኢትዮጵያ አንድነታችንን መጠበቅና ማጠናከር የግድ ይለናል” ሲሉ አበክረዋል።
ከህዳሴ ግድብ ምርቃት ጎን ለጎንም “በየቀኑ ስለሚጠፋው የዜጎቻችን ህይወት፣ ስለሚፈሰው ደምና ስለምታነባው ኢትዮጵያዊ እናት፣ በጥቅሉ ስለአገራችን ሠላምና ደህንነት ቆም ብለን ልናስብበትና በጋራ መቋጫ ልናበጅለት ግድ ይለናል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቶ ለማ በመልዕክታቸውም የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክቱን አስጀምረው በማጠናቀቅ ሂደት ውስጥ አስተዋጽኦ የነበራቸው የአገራችን መሪዎችና ባለሙያዎች ሁሉ እንደየድርሻቸውና አስተዋጽኦአቸው መጠን ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
መጋቢት 24/2003 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከ14 ዓመታት በኋላ ትናንት ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የቀጠናው ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
ይህን ተከትሎ የሀገራት መሪዎች፣ የተቋማት የስራ ሀላፊዎች እና በርካታ ወገኖች የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
Via: አዲስ ስታንዳርድ

10 comments
ኦቦ ለማ ምርጥ ሰዉ
አቶ??
ወንበርህን ለአንድ ተራ ሰው ሰትጠህ ድምፅህን አጠፋህ
,አንተንም ታሪክ አይረሳህም ሁሌም ስለሠላም ያለሄውን አቋም እኛም እናከብርሃለን
አንተ እኮ ነህ መርቀህ ያስጀመርከው አስመሳዩ 👎👎👎
Our hero❤❤😍
ኢትዮጵያዊ 🙏
እውነተኛ ኢትዮጵያዊ Dor ለማ መገርሳ
አዋላጅ አንተነህ አሁን ቆጨህ?
ከታች እስከ ፌዴራል የጋራ ህግ የለለበት ሀገር ሆነው የኢትዮጵያ ከፍታ በመከራ የታጀበ ሆኑዋል። ፈጣሪ ለአሁኑ አመራር ልቦና እንድሰጠው እንለምናለን!!